አትለፈኝ (Atelefegn) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ከአንተ ፡ ወደ ፡ ማን ፡ እሄዳለሁ ፡ ማን ፡ አላት ፡ ነፍሴ
ለሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ አንተ ፡ አይደለህ ፡ ወይ ፡ ክብሬ ፡ ሞገሴ
ያለአንተ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ከውኃ እንደወጣ ፡ ዓሣ ፡ ያኔ ፡ እጠፋለሁ

ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መኖር ፡ ይሻለኛል
ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ አልፈልግም ፡ ላጣህ ፡ አንተን
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መኖር ፡ ይሻለኛል
ሰላሜ ፡ ነህ ፡ አልፈልግም ፡ ላጣህ ፡ አንተን

ዋናዬ ፡ ነህ ፡ ዋናዪ ፡ ነህ ፡ እኔስ ፡ አልጣህ
ዋናዬ ፡ ነህ ፡ ዋናዬ ፡ ነህ ፡ እኔስ ፡ አልጣህ

በሰፈሬ ፡ በመንደሬ ፡ ድል ፡ ልትሰጠን ፡ ስትመጣ
ጉብኝትህ ፡ እንዳያልፈኝ ፡ በስፍራዬ ፡ እንዳልታጣ
ጠብቅሃለሁ ፡ ተሰናድቼ ፡ ቤቴን ፡ መንደሬን ፡ አጸዳድቼ
ጠብቅሃለሁ ፡ ተሰናድቼ ፡ ቤቴን ፡ መንገዴን ፡ አጸዳድቼ

ጠብቅሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ተሰናድቼ
ቤቴን ፡ ጓዳዬን ፡ አሃ ፡ አጽዳድቼ (፪x)

አምላኬ ፡ ፊትህን ፡ እሻለሁ ፡ በዚህ ፡ ቦታ
እንድትዳስሰኝ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ
አትለፈኝ ፡ ጌታ ፡ አትለፈኝ ፡ ጌታ
አትለፈኝ ፡ ኦሆ ፡ አትለፈኝ ፡ ኦሃ
አትለፈኝ ፡ አባ ፡ አትለፈኝ ፡ ኦሆ

ጌታ ፡ ጌታ ፡ አትለፈኝ ፡ አትለፈኝ
ጸሎቴ ፡ ጩሄቴ ፡ ሞገስ ፡ ያግኝህ ፡ ሞገስ ፡ ያግኝህ
አትለፈኝ ፡ አትለፈኝ ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ሕይወት ፡ ሕይወት ፡ የለኝም
አትተወኝ ፡ አትተወኝ ፡ ያለአንተ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ አዎ

ልቤ ፡ እያወቀው ፡ መውደቅ ፡ መሸነፌን
የግብዝነቴ ፡ ታገለው ፡ መንፈሴ
አስመስሎ ፡ መኖር ፡ በቃ ፡ ይበቃኛል
ለውጠኝ ፡ አባቴ ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል
ይሻለኛል ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል (፪x)

አትለፈኝ ፡ ኦሆ ፡ አትለፈኝ ፡ ኦሆ

ሽንገላ ፡ ተሞልቶ ፡ አቤት ፡ አንደበቴ
ጉልበቴን ፡ ጨረስኩት ፡ ባዶ ፡ ሆነ ፡ ቤቴ
ያው ፡ ከነድካሜ ፡ ፊትህ ፡ ወድቄያለሁ
ለፈቃዴ ፡ አትስጠኝ ፡ እለመንሃለሁ

ሁሉን ፡ ልጣ ፡ አንተን ፡ ከማጣ ፡ አባ ፡ አንተን ፡ ከማጣ
ሁሉ ፡ ይቅር ፡ አንተ ፡ ከምትቀር ፡ አባ ፡ አንተ ፡ ከምትቀር (፪x)

አንተው ፡ ትሻለኛለህ
አንተው ፡ ትበቃኛለህ
ነፍሴን ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቻለሁ
አባ ፡ ተማርኬያለሁ
ተማርኬያለሁ ፡ ተማርኬያለሁ (፪x)