አሳመረልኝ (Asamerelegn) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ጓዳዬ ፡ ሆኜ ፡ የልቤን
ነገርኩት ፡ የውስጥ ፡ የሆዴን
በጊዜው ፡ ጌታ ፡ መጣና
አሳመረልኝ ፡ ድንቅ ፡ አረገና (፪x)

አሳመረለኝ ፡ አሃሃ ፡ ድንቅ ፡ አረገና (፪x)
አሳመረልኝ ፡ አዎ ፡ ድንቅ ፡ አረገና (፪x)

ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የራራልኝ ፡ የራራልኝ
ያንን ፡ ዘመን ፡ ያሻገረኝ ፡ ያሻገረኝ
ዘምራለሁ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ
ያረገልኝ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
ይዤ ፡ ልግባ ፡ ማደሪያው
ምሥጋናዬ ፡ ያውድ ፡ መዓዛው
ያውድ ፡ መዐዛው ፡ ይብዛ ፡ ዕልልታው (፪x)

በማደሪያው ፡ ምሥጋናው
በማደሪያው ፡ ዕልልታው
በመቅደሱ ፡ ምሥጋናው
በመቅደሱ ፡ ዕልልታው

አላስኬድ ፡ ያሉኝ ፡ ከፊቴ ፡ ቆመው
ህልሜን ፡ ተስፋዬን ፡ ሁሉ ፡ አጨልመው
መንገዴን ፡ ዘግተው ፡ በቆሙት ፡ ላይ
ቁጣው ፡ ነደደ ፡ መጣ ፡ ከላይ
በበቀል ፡ እሳት ፡ ወረደባቸው
ግድብ ፡ እንዲፈርስ ፡ አፈረሳቸው
አፈረሳቸው (፪x)

እኔማ ፡ ጌታን ፡ ብዬ
አላፈርኩ ፡ እርሱን ፡ ብዬ
ጨመረ ፡ ምሥጋናዬ (፪x)
ጨመረ ፡ ምሥጋናዬ (፪x)

ለእንቆቅልሼ ፡ መፍትሄ ፡ ሰጥቶ
የሚያስፈነድቅ ፡ የልብን ፡ ሞልቶ
ከአፉ ፡ ከወጣ ፡ ስልጣን ፡ ያለው ፡ ቃል
የማይሆን ፡ የለም ፡ ያለው ፡ ይሆናል
እንደርሱ ፡ ማነው ፡ ተዐምረኛ
እንቆቅልሼን ፡ ፈቶ ፡ አሳየኛ
ፈቶ ፡ አሳየኛ (፪x)

ተሰርቶልኝ ፡ ስራዬ
ሃዘን ፡ ሄዷል ፡ ከላዬ
ቤቴን ፡ ሞላው ፡ ደስታ
ልዘምር ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፪x)
ልዘምር ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፬x)

ፍጥረት ፡ በስራህ ፡ የሚገዙለት
ማዕበል ፡ ወጀቡ ፡ የሚታዘዙለት
ይናገር ፡ እንጁ ፡ ይበል ፡ ንጉሡ
ማይሰማው ፡ የለም ፡ ሕያው ፡ ግዑዙ
እርሱ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ዐይኔ ፡ አይቶታል
ማይቻለውን ፡ ሁሉ ፡ ችሎታል
ሁሉ ፡ ችሎታል (፪x)

እኔማ ፡ ጌታን ፡ ብዬ
አላፈርኩ ፡ እርሱን ፡ ብዬ
ጨመረ ፡ ምሥጋናዬ (፪x)
ጨመረ ፡ ምሥጋናዬ

ተሰርቶልኝ ፡ ስራዬ
ሃዘን ፡ ሄዷል ፡ ከላዬ
ቤቴን ፡ ሞላው ፡ ደስታ
ልዘምር ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፪x)
ልዘምር ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፰x)