አንቃኝ (Anqagn) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 4.jpg


(4)

ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር
(Qedesena LeEgziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ኖሬ ፡ አንተን ፡ አስከብሬ ፡ ፍሬን ፡ እንዳፈራ
ነበረ ፡ ምኞትህ ፡ ያሁሉ ፡ ልፋትህ ፡ እኔን ፡ ስትሰራ
ቅጠሉ ፡ እንዳማረ ፡ ግን ፡ ፍሬ ፡ እንደሌለው ፡ በለስ ፡ ሆኛለሁ
ጥቂት ፡ ታገሰኝ ፡ አንድ ፡ እድል ፡ ስጠኝ ፡ ፊትህ ፡ ወድቄያለሁ

እንዳትተወኝ ፡ እማጸናለሁ
ከተውከኝማ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ (፪x)
ባጠፋ ፡ እንኳ ፡ ቆንጥጠህ ፡ መልሰኝ
ብበድልህ ፡ እንኳ ፡ ገስጸህ ፡ መልሰኝ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያለአንተ ፡ ማን ፡ አለኝ

ድንጋዩን ፡ ልቤን ፡ ባክህ ፡ አውጣልኝ ፡ አባ ፡ እባክህ ፡ አውጣልኝ
አዲስን ፡ መንፈስ ፡ በውስጤ ፡ አኑርልኝ ፡ ጌታ ፡ በውስጤ ፡ አኑርልኝ
ድምጽህን ፡ ስሰማ ፡ አው ፡ አልሁን ፡ እልኸኛ
ቸል ፡ ብዬ ፡ እንዳልጠፋ ፡ አባ ፡ እባክህ ፡ አንቃኛ
እባክህ ፡ አንቃኛ (፪x)

የሰጠኸኝን ፡ ያንን ፡ አደራ ፡ ያንን ፡ መክሊት
ነበር ፡ ነቅቼ ፡ እንድጠብቅህ ፡ ብዙ ፡ አትርፌበት
ምንም ፡ ሳልሰራ ፡ እንደቀበርኩት ፡ ምጻትህ ፡ ቀርቧል
አንቃኝ ፡ ጌታዬ ፡ ከስንፍናዬ ፡ ኋላ ፡ እንዳልጣል

ዝም ፡ እንዳትለኝ ፡ እማጸናለሁ
ዝም ፡ ካልክማ ፡ እኔ ፡ እፈራለሁ (፪x)
አባ ፡ አድነኝ ፡ ከቁጣህ ፡ አድነኝ
አድነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አድነኝ

ለጠፊው ፡ ዓለም ፡ ስጥር ፡ ስለፋ ፡ ጊዜዬ ፡ አልቆ
ሠማያዊውን ፡ የዘለዓለሙን ፡ ልቤ ፡ ዘንግቶ
ኃይሌ ፡ ተሟጦ ፡ ዘይቴ ፡ አልቆ ፡ ባዶ ፡ ሆኛለሁ
ማረኝ ፡ አባቴ ፡ ገባኝ ፡ ጥፋቴ ፡ እመለሳለሁ

እኔን ፡ ለምኞቴ ፡ አትስጠኝ ፡ ጌታዬ ፡ አትስጠኝ ፡ ጌታዬ
እኔን ፡ ለሥጋዬ ፡ አትስጠኝ ፡ አባዬ ፡ አጽጠኝ ፡ አባዬ

እግዚአብሔርን ፡ መፍራት ፡ ጠፍቶ ፡ የለም ፡ ወይ
ምኞቱን ፡ የሚያረግ ፡ ሞልቶ ፡ የለም ፡ ወይ
ባክህ ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ አባ ፡ አስተዋይ ፡ አድርገኝ
ወደ ፡ ጽድቅ ፡ ጐዳና ፡ አሃ ፡ እግሬን ፡ መልስልኝ
አድነኝ ፡ አባ ፡ አድነኝ ፡ ኢየሱስ
አድነኝ ፡ ጌታ ፡ አድነኝ ፡ አን..