ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው (Zariem Heyaw New) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 1.jpg


(1)

ባለውለታዬ ፡ ጌታ
(Baleweletayie Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 8:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ማንም ፡ ያልፈታውን ፡ ማኅተም ፡ የፈታህ
በትንሳዔው ፡ ጉልበት ፡ ሁሉንም ፡ የረታህ
በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ አለ ፡ መቃብር ፡ ፈንቅሎ
ገና ፡ ሁሉን ፡ ይገዛል ፡ ዳግም ፡ ተመልሶ (፪x)

ኢየሱስ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
ኢየሱስ ፡ በትንሳኤው ፡ ጉልበት
ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ የረታ

ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው
ለዚህ ፡ ሥም ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ማይገዛው
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካል
አጋንንት ፡ ለሥሙ ፡ ይንቀጠቀጣል
ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ኢሄ ፡ አምላካችን
ገናናው ፡ ኢየሱስ ፡ መከታ ፡ ጋሻችን (፪x)
መከታ ፡ ጋሻችን (፪x)

ሰባቱን ፡ ከዋክብት ፡ በእጁ ፡ የያዘ
በወርቅ ፡ መታጠቂያ ፡ ደረቱን ፡ የታጠቀ
እንደ ፡ እሳት ፡ ነበልባል ፡ ዓይኖቹ ፡ ይህ ፡ ጌታ
ፊቱም ፡ እንደፀሐይ ፡ ደምቆ ፡ የሚያበራ (፪x)

ኢየሱስ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
ኢየሱስ ፡ በትንሳኤው ፡ ጉልበት
ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ የረታ

ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው
ለዚህ ፡ ሥም ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ማይገዛው
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካል
አጋንንት ፡ ለሥሙ ፡ ይንቀጠቀጣል
ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ኢሄ ፡ አምላካችን
ገናናው ፡ ኢየሱስ ፡ መከታ ፡ ጋሻችን (፪x)
መከታ ፡ ጋሻችን (፪x)

የመጀመሪያና ፡ መጨረሻ ፡ እርሱ ፡ ነው
ዘለዓለም ፡ ያው ፡ ሆኖ ፡ በላይ ፡ የሚኖረው
የመክፈት ፡ የመዝጋት ፡ ሥልጣን ፡ ሁሉ ፡ የእርሱ
በሆታ ፡ በዕልልታ ፡ ኢየሱስን ፡ አንግሱ ፡ ስሙን ፡ አወድሱ

ኢየሱስ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ
ኢየሱስ ፡ በትንሳኤው ፡ ጉልበት
ኢየሱስ ፡ ሁሉንም ፡ የረታ

ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው
ለዚህ ፡ ሥም ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ማይገዛው
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ይንበረከካል
አጋንንት ፡ ለሥሙ ፡ ይንቀጠቀጣል
ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ኢሄ ፡ አምላካችን
ገናናው ፡ ኢየሱስ ፡ መከታ ፡ ጋሻችን (፪x)
መከታ ፡ ጋሻችን (፪x)

ውሃን ፡ አጣፈጠ ፡ ማዕበሉን ፡ አዘዘ
በሙት ፡ በሲኦል ፡ ላይ ፡ ሥልጣኑን ፡ አሳየ
ምን ፡ አለ ፡ በምድር ፡ ለእርሱ ፡ የተሳነው
እኛም ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

አቤት (፬x) ፡ አቤት ፡ እንደኢየሱስ
ማነው ፡ አቤት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬን
እርሱን ፡ ማነው

(ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማነው
(ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ውዴ ፡ ማነው
(ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማነው
(ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ውዴ ፡ ማነው
(ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማነው
(ኧረ ፡ ማነው) ፡ እርሱ ፡ መድሃኒት ፡ ነው
(ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማነው
(ኧረ ፡ ማነው) ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማነው (፫x)