Yosef Bekele/Baleweletayie Gieta/Weletaw Bezabegn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ዮሴፍ በቀለ ርዕስ ውለታው በዛብኝ አልበም ባለውለታዬ ጌታ

ዛሬ ልጅ ተብዬ ክብርን አግኝቻለሁ የቀድሞ ኑሮዬን ረስቼዋለሁ ታሪኬን ለውጠህ ሰው አድርጐ አቆመኝ የመረጥኩህ ልጄ እስራኤል ሆይ አለኝ የመረጥኩህ ልጄ የምወድህ ሆይ አለኝ

አዝ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው ይድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (፪x)

በክርስትናዬ እድሜን ቆጥሬያለሁ በልማዳዊ ሕይወት ተመላልሻለሁ ዛሬ ግን ኢየሱስ ነፍሴ አወቀችህ አምላኬ ጌታዬ ውዴ ነህ አለችህ አምላኬ ጌታዬ አባቴ አለችህ

አዝ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (፪x)

የስጋዬን ሳስብ እንዲያው ስቅበዘበዝ ጠላት ቤቴ ገብቶ ምርኮን ሲበዘብዝ እርሱ ግን ጌታዬ አሰበኝ ለአንድ አፍታ ኃይሌም ተመለሰ ጠላቴም ተረታ ኃይሌም ተመለሰ ይክበር የእኔ ጌታ

አዝ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ