መስቀልህ ፡ ስር (Mesqeleh Ser) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 1.jpg


(1)

ባለውለታዬ ፡ ጌታ
(Baleweletayie Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

አዝ፦ እስኪ ፡ አዝ፦ እስኪ ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ሸክሜን ፡ ልጣለው (፪x) ፡ አዎ
ማረፊያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰላሜ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እረፍቴ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ አዎ
ሁሉ ፡ ያለቀበትን ፡ መስቀልህን ፡ እያየሁ (፪x) ፡ ኦሆ
ያኔ ፡ መከራዬን ፡ ችግሬን ፡ እረሳለሁ ፡ ጭንቀቴን ፡ እረሳለሁ ፡ አዎ

በቀራኒዮ ፡ ላይ ፡ ስለእኔ ፡ ተሰቅለህ (፪x) ፡ ኦሆ
አንተ ፡ ከእኔ ፡ ፈንታ ፡ እርጉም ፡ ሰው ፡ ተብለህ ( ፡ ስር ፡ ሸክሜን ፡ ልጣለው (፪x) ፡ አዎ
ማረፊያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰላሜ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እረፍቴ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ አዎ
ሁሉ ፡ ያለቀበትን ፡ መስቀልህን ፡ እያየሁ (፪x) ፡ ኦሆ
ያኔ ፡ መከራዬን ፡ ችግሬን ፡ እረሳለሁ ፡ ጭንቀቴን ፡ እረሳለሁ ፡ አዎ

በቀራኒዮ ፡ ላይ ፡ ስለእኔ ፡ ተሰቅለህ (፪x) ፡ ኦሆ
አንተ ፡ በእኔ ፡ ፈንታ ፡ እርጉም ፡ ሰው ፡ ተብለህ (፪x) ፡ አዎ
ተፈጸመ ፡ ብለህ ፡ ሁሉንም ፡ ጨረስከው (፪x) ፡ ኦሆ
ለዘለዓለሙ ፡ መርገሜን ፡ ወሰድከው ፡ እዳዬን ፡ ከፈልከው ፡ አዎ

መራራውን ፡ ጽዋ ፡ ጠጣህ ፡ በእኔ ፡ ፈንታ
የታሰርኩበትም ፡ ሰንሰለት ፡ ተፈታ
መስቀልህ ፡ ስር ፡ አለሁ ፡ ጥያቄዬን ፡ ይዤ
ከላዬ ፡ ውሰደው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ

አዝ፦ እስኪ ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ሸክሜን ፡ ልጣለው (፪x) ፡ አዎ
ማረፊያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰላሜ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እረፍቴ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ አዎ
ሁሉ ፡ ያለቀበትን ፡ መስቀልህን ፡ እያየሁ (፪x) ፡ ኦሆ
ያኔ ፡ መከራዬን ፡ ችግሬን ፡ እረሳለሁ ፡ ጭንቀቴን ፡ እረሳለሁ ፡ አዎ

ሸክም ፡ ሲያንገላታኝ ፡ ቀንበር ፡ ሲከብድብኝ (፪x) ፡ ኦሆ
ጨለማው ፡ በርትቶ ፡ መሄጃው ፡ ሲጠፋኝ (፪x) ፡ አዎ
ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ ስጠራህ ፡ ጌታዬ (፪x) ፡ ኦሆ
ፈጥነህ ፡ ድረስና ፡ ስበርው ፡ ከላዬ ፡ ቀንበሩን ፡ ከላዬ ፡ አዎ

ከእናት ፡ ከአባት ፡ በላይ ፡ ቀርበህ ፡ ምትረዳኝ
ሚስጢሬን ፡ ተካፋይ ፡ ማን ፡ እንዳንተ ፡ ጌታ
ገበናዬን ፡ ሸፋኝ ፡ ሚስጢረኛዬ ፡ ነህ
ከማንም ፡ ከምንም ፡ ትበልጥብኛለህ
ከታላቁ ፡ ስፍራ ፡ ከእዛ ፡ የወረድከው
ፍቅር ፡ ያስገደደህ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪X)
ችግሬን ፡ ሚረዳኝ ፡ እንዳንተ ፡ የለምና
ሁሉን ፡ ነግርሃለሁ ፡ ፊትህ ፡ እደፋና

"እናንተ ፡ ደካሞች
ሸክም ፡ የከበዳችሁ ፡ ሁሉ
ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ እኔም ፡ አሳርፋቹሃለሁ
ኑ ፡ እኔም ፡ አሳርፋቹሃለሁ" [1]

  1. የማቴዎስ ፡ ወንጌል ፲፩ ፡ ፳፰ (Matthew 11:28)