ላመስግነው (Lamesgenew) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 1.jpg


(1)

ባለውለታዬ ፡ ጌታ
(Baleweletayie Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው
የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን
ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን
ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም
ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው
ላመስግነው

የኃጢአቴን ፡ ቀንበር ፡ በላዬ ፡ ያለውን
ሰበረው ፡ ከላዬ ፡ ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ጌታዬ
ቀደደው ፡ የመርገም ፡ ጨርቄን
አራቀው ፡ ውዴ ፡ አበሳዬን
አነጻኝ ፡ ጌታ ፡ በደሙ
በልቤ ፡ ሞላ ፡ ሰላሙን
ላመስግነው

አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው
የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን
ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን
ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም
ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው
ላመስግነው

ዙሪያዬን ፡ ከቦኝ ፡ ጠላቴ
ሚረዳኝ ፡ ባጣሁኝ ፡ ጊዜ
በጭንቄ ፡ ሳለሁ ፡ ደረሰ
እምባዬን ፡ ከዓይኔ ፡ አበሰ
አሰበኝ ፡ ከአሪያም ፡ አምላኬ
ጋሻዬ ፡ ሆነ ፡ ምርኩዜ
ረገጠው ፡ ያስጨነቀኝን
አሳደደው ፡ ያሳደደኝን
ላመስግነው

አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው
የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን
ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን
ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም
ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው
ላመስግነው

ምስቅልቅል ፡ ያለው ፡ ሕይወቴን
የባዘነችውን ፡ ነፍሴን
ኢየሱሴ ፡ ደርሶ ፡ አጣፈጠው
መራራውን ፡ ኑሮ ፡ ለወጠው
ሙሉ ፡ አደረገኝ ፡ ወዳጄ
አወጣኝም ፡ ከኩነኔ
ምን ፡ ልክፈለው ፡ ለዚህ ፡ ጌታ
ላክብረው ፡ ክብሬን ፡ በዕልልታ
ላመስግነው

አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው
የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን
ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን
ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም
ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው
ላመስግነው

ሰው ፡ የጠላውን ፡ ሃሳቢ
የተገፋውን ፡ ሰብሳቢ
ለቸገረው ፡ ፈጥኖ ፡ ደራሽ
ለሚያነባ ፡ እምባውን ፡ አባሽ
አንተ ፡ ነህ ፡ እውነተኛ ፡ ወዳጅ
ማትለይ ፡ ሁሌም ፡ ማትሰለች
ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ
ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ታኮራለህ
ላመስግንህ

አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው
የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን
ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን
ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም
ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው
ላመስግነው