ሃሌሉያ (Hallelujah) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 1.jpg


(1)

ባለውለታዬ ፡ ጌታ
(Baleweletayie Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

አዝ፦ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)

ዛሬም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ነገም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
ሁሌም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ አዎ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ኃያል ፡ ነህ ፡ ማንንም ፡ አትንቅም
ማስተዋል ፡ ጥበብህ ፡ አይመረመርም
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ ሁሌ ፡ ያመስግኑህ
የሚፈሩህ ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይገዙልህ (፫x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)

ዛሬም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ነገም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
ሁሌም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ አዎ (፪x)

ዙፋንህ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ የማትነቃነቅ
ሽምግልና ፡ አያውቅህ ፡ ከቶ ፡ አትለዋወጥ
ጥንት ፡ እንደሰራኸው ፡ ዛሬም ፡ ትሰራለህ
አትደክም ፡ አትታክት ፡ አንተ ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ (፫x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)

ዛሬም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ነገም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
ሁሌም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ አዎ (፪x)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ ከምድር ፡ በታች ፡ ሁሉ
ለታላቅነትህ ፡ ፍጥረታት ፡ ይስገዱ
ያመስግኑህ ፡ ዛሬ ፡ ያንግሱህ ፡ በዕልልታ
ንጉሥ ፡ ነህ ፡ ዘለዓለም ፡ የሰራዊት ፡ ጌታ (፫x)

አዝ፦ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)

ዛሬም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ነገም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ
ሁሌም ፡ ተመስገን/ተባረክ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ አዎ (፪x)