Yosef Bekele/Baleweletayie Gieta/Gashayie New Ersu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ዮሴፍ ፡ በቀለ ርዕስ ጋሻዬ ነው እርሱ አልበም ባለውለታዬ ጌታ

ሰላሜ (ሰላሜ) ሰላሜ (ኦ ሰላሜ) ሰላሜ አዎን

ኢየሱስ ሰላሜ (፪x)
ሰላም አንተ ነህ ሰላሜ
ሰላም የሕይወቴ ማረፊያ
ሰላም በአንተ ደስ ይለኛል
ሰላም ሕይወቴ እኮ ረካ
ረካ ረካ ረካ አዎ
ባጣ አይጨንቀኝም በእርሱ እጽናናለሁ
ብራብ አይገደኝም ክብሩን ሳይ እጠግባለሁ
ቢጠማኝም እንኳ ፍፁም እርካታዬ
ኢየሱሴ ነው ለእኔስ የሕይወት ውሃዬ
አዝ
ኢየሱስ ሰላሜ ነው ማን ይወስድብኛል
ከብርና ከወርቅ ሁሉ ይበልጥብኛል
እርካታ ለነፍሴ መጽናኛዬም እርሱ
ድጋፌ ምርኩዜ ጋሻዬ ነው እርሱ
ጋሻዬ ነው እርሱ (፫x) አዎን ጋሻዬ ነው እርሱ
ጋሻዬ ነው እርሱ (፫x) ጌታ ጋሻዬ ነው እርሱ
እርሱ ውበትን አጥቶ ውበት የሆነልኝ

ደም ግባቱን አጥቶ ደም ግባቱን ሰጠኝ በእርሱ የተነሳ ሞገስ አግኝቻለሁ በተራራ ጫፍ ላይ ቤቴን መስርቻለሁ

አዝ
በብርና በወርቅ ወይም በሃብት ብዛት
በኃይሌም አይደለም ሰላም ያገኘሁት
ከአብ ዘንድ ተልኮ እኔን ያሳረፈኝ
ኢየሱሴ እኮ ነው ሰላሜ የሆነኝ
አዝ
ስለ እኔ በደል እርሱ ተንገላቶ
አሳረፈኝ ውዴ አበሳዬን ወስዶ
ዛሬማ ኢየሱሴ ቅርሴ ሆኖልኛል
በሰማዩ ስፍራ በመንፈስ ባርኮኛል
አዝ
ማዕበሉ ቢያናውጥ ወጀቡ ቢበዛም
ሁሉ ባዶ ቢሆን ኑሮ ባይሳካም
እኔስ አባብዬ ተንተርሻለሁኝ
ከቶ አልናወጥም ተሸሽጌያለሁኝ
ሰላሜ (ሰላሜ) ሰላሜ (ኦ ሰላሜ) ሰላሜ አዎን ኢየሱስ ሰላሜ
ሰላም አንተ ነህ ሰላሜ
ሰላም የሕይወቴ ማረፊያ
ሰላም በአንተ ደስ ይለኛል
ሰላም ሕይወቴ እኮ ረካ
ረካ ረካ ረካ አዎ