ቤተክርስቲያን (Bietekrestiyan) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 1.jpg


(1)

ባለውለታዬ ፡ ጌታ
(Baleweletayie Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

አዝ፦ ቤተክርስቲያን ፡ ሙሽራይቱ
ሙሽራሽ ፡ ሊመጣ ፡ ጊዜው ፡ አይደለም ፡ ወይ
አጊጠሽ ፡ ጠብቂ ፡ ተዘጋጂ ፡ ቶሎ
ሙሽራሽ ፡ ይመጣል ፡ መላዕክት ፡ አስከትሎ
በመላዕክት ፡ ታጅቦ ፡ ኦሆ

የቀድሞ ፡ ፍቅርሽን ፡ አድሺ ፡ በጊዜ
ከአንቺ ፡ ይወገዱ ፡ ድካም ፡ ድንዛዜ
ንቂ ፡ መብራት ፡ አብሪ ፡ ተዘጋጂ ፡ ፈጥነሽ
ጠብቂው ፡ ኢየሱስን ፡ ጌጠኛ ፡ ልብስ ፡ ለብሰሽ
ያማረ ፡ ልብስ ፡ ለብሰሽ ፡ አዎ

በራድ ፡ ወይም ፡ ትኩስ ፡ ከቶም ፡ አይደለሽ
እስካሁን ፡ ኖረሻል ፡ እንዲያው ፡ ለብ ፡ ብለሽ
ትምክህትሽን ፡ ጣዪ ፡ አትበይ ፡ ሁሉ ፡ አለኝ
ኋላ ፡ እንዳታጪ ፡ ሊመጣ ፡ ያለውን
ሊገለጥ ፡ ያለውን ፡ አዎ

አዝ፦ ቤተክርስቲያን ፡ ሙሽራይቱ
ሙሽራሽ ፡ ሊመጣ ፡ ጊዜው ፡ አይደለም ፡ ወይ
አጊጠሽ ፡ ጠብቂ ፡ ተዘጋጂ ፡ ቶሎ
ሙሽራሽ ፡ ይመጣል ፡ መላዕክት ፡ አስከትሎ
በመላዕክት ፡ ታጅቦ ፡ ኦሆ

በፈሰሰልሽ ፡ ደም ፡ ጉድፍሽኝ ፡ አጥሪ
ቀን ፡ ሳለ ፡ በጊዜ ፡ ራስሽን ፡ መርምሪ
ኩል ፡ ግዢ ፡ ከጌታ ፡ ዓይንሽ ፡ ይከፈታል
የጐደለሽ ፡ ሁሉ ፡ ያኔ ፡ ይታይሻል
ያኔ ፡ ይታይሻል ፡ አዎ

ኩራዝሽን ፡ አብሪ ፡ ዘይቱንም ፡ ግዢ
ምንም ፡ እንዳይጐድልሽ ፡ ትጊ ፡ ተጠንቀቂ
የምትጠብቂው ፡ ሙሽራ ፡ ይመጣል
አታፍሪም ፡ ዘለዓለም ፡ እርሱም ፡ ያከብርሻል
ከፍም ፡ ያደርግሻል ፡ አዎ

ድል ፡ ለነሣው ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ በዙፋን ፡ ላይ ፡ ይቀመጥ ፡ ዘንድ ፡ ይሰጠዋል
መንፈስ ፡ ለአብያተ ፡ ክርስቲያናት ፡ የሚለውን ፡ ጆሮ ፡ ያለው ፡ ይስማ [1]

  1. የዮሐንስ ፡ ራዕይ 3 ፡ 21 (Revelations 3:21)