በማለዳ ፡ ምሥጋና (Bemaleda Mesgana) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 1.jpg


(1)

ባለውለታዬ ፡ ጌታ
(Baleweletayie Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
የውስጥ ፡ ብሶቴን ፡ ጭንቄን ፡ ሚያሟላ
እድል ፡ ፈንታዬ ፡ አንተው ፡ ነህና
አዋይሃለሁ ፡ አጫውትሃለሁ
ማን ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x)

ዞሬያለሁኝ ፡ በዓለም ፡ ተስፋ ፡ አገኝ ፡ መስሎኝ
በከንቱ ፡ ዘመኔን ፡ እንዲያው ፡ ጨረስኩኝ
የምታዛልቀኝ ፡ አንተው ፡ ብቻ ፡ ነህ
ተረድቻለሁ ፡ ና
እምባዬን ፡ አብስ ፡ ተስፋዬን ፡ አድስ

ከማህጸን ፡ ጀምሮ ፡ ተሸክመኸኛል
እንደ ፡ ልጅ ፡ አባብለህ ፡ አሳድገኸኛል
ከአንተ ፡ ወዲያ ፡ ለእኔ ፡ የለኝም ፡ የማውቀው
ኧረ ፡ ፊትህ ፡ ወድቄ ፡ እማጸንሃለሁ

ጌታ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ
ጌታ ፡ አለሁልህ ፡ በለኝና
እስኪ ፡ ልረፍ ፡ ድምጽህን ፡ ልስማ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
መጠጊያዬን ፡ አውቃለሁ

አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
የውስጥ ፡ ብሶቴን ፡ ጭንቄን ፡ ሚያሟላ
እድል ፡ ፈንታዬ ፡ አንተው ፡ ነህና
አዋይሃለሁ ፡ አጫውትሃለሁ
ማን ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x)

ወደ ፡ ቀኝ ፡ ወደ ፡ ግራ ፡ ተመለከትኩኝ
ተስፋ ፡ የሚሆነኝ ፡ አንድም ፡ አጣሁኝ
መሸሸጊያዬ ፡ ለእኔ ፡ መድሃኒት
ለነፍሴ ፡ ጌታ ፡ ና
ከእስራት ፡ ፍታኝ ፡ ልጄ ፡ ነህ ፡ በለኝ

ብዙ ፡ ነገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ የማጫውትህ
የልቤን ፡ የውስጤን ፡ ሁሉንም ፡ ልንገርህ ፡ ኢየሱስ
ነፍሴ ፡ በእጅህ ፡ ናት ፡ መላው ፡ አካላቴ
ፈቃድህ ፡ ይሁንልኝ ፡ ያልከው ፡ በሕይወቴ

ጌታ ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ ማረፊያ
ጌታ ፡ አለሁልህ ፡ በለኝና
እስኪ ፡ ልረፍ ፡ ድምጽህን ፡ ልስማ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
መጠጊያዬን ፡ አውቃለሁ

አዝ፦ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
የውስጥ ፡ ብሶቴን ፡ ጭንቄን ፡ ሚያሟላ
እድል ፡ ፈንታዬ ፡ አንተው ፡ ነህና
አዋይሃለሁ ፡ አጫውትሃለሁ
ማን ፡ አለኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x)