Yosef Bekele/Baleweletayie Gieta/Baleweletayie Eyesus

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ዮሴፍ በቀለ ርዕስ ባለውለታዬ ኢየሱስ አልበም ባለውለታዬ ጌታ

አዝ ውለታህ አሃሃ ውለታህ ብዙ ብዙ
አንተ ጌታዬ ባለውለታዬ (፪x)
ባለውለታዬ ጌታ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)
ባለውለታዬ ኢየሱስ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)

ኢየሱሴ ስለእኔ ያኔ የቃተትከው
ከኃጢአት በሽታ እኔን ለማዳን ነው
በእኔ ፈንታ ቆስለህ እኔን ፈወስከኝ
ውለታህን ሳስብ እጅግ ደነቀኝ
ተመስገን አልኩኝ

አዝ
ውለታህ አሃሃ ውለታህ ብዙ ብዙ
አንተ ጌታዬ ባለውለታዬ (፪x)
ባለውለታዬ ጌታ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)
ባለውለታዬ ኢየሱስ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)

ጠላቴ በእኔ ላይ ምሽግን መሽጐ
ነፍሴን ሊያጠፋት ወጥመዱን ዘርግቶ
የጠላቴን ወጥመድን ሰበርክልኝና
ዛሬ ይሄው አቆምከኝ በድል በምሥጋና
መመኪያዬ ገናና

አዝ ውለታህ አሃሃ ውለታህ ብዙ ብዙ
አንተ ጌታዬ ባለውለታዬ (፪x)
ባለውለታዬ ጌታ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)
ባለውለታዬ ኢየሱስ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)

ለነፍሴ ዋልክላት እጅግ ብዙ ውለታ
ወደደችህ ነፍሴም አመጣች ስጦታ
እንካ ተቀበላት የአፏን ዝማሬ
ሰው ሆናለች በአንተ አምሮባታል ዛሬ
ታክብርህ ፡ መድህኔ

አዝ ውለታህ አሃሃ ውለታህ ብዙ ብዙ
አንተ ጌታዬ (ኤሄ) ባለውለታዬ (፪x)
ባለውለታዬ ጌታ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)
ባለውለታዬ ኢየሱስ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)

ቀስት ከሚገትሩ ያኔ የታደግካት
ከሚያሳድዷት ሁሉ የሰወርካት
ክብሯን ሁሉ ጥላ ታሸበሽባለች
ለአምላኬ ውለታ ያንስበታል እያለች
ትባርክሃለች

አዝ ውለታህ አሃሃ ውለታህ ብዙ ብዙ
አንተ ጌታዬ (ኤሄ) ባለውለታዬ (፪x)
ባለውለታዬ ጌታ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)
ባለውለታዬ ኢየሱስ ባለውለታዬ (አሃ)
ባለውለታዬ እንካ ምሥጋናዬን (አዎ)

  ከክፉ ፍላጻ ጋሻ መከታዬ
መመኪያዬ ኢየሱስ ጥላ ከለላዬ
ውለታህን ከቶ እንዴት እረሳለሁ
እስከዘለዓለም እቀኝልሃለሁ
ሌላ ምን እላለሁ

  አዝ እኔስ በአንተ ጌታ ደስ ይለኛል (አዎ)
ደስ ይለኛል (እሰይ) ደስ ይለኛል (አዎ)
ጌት በማዳንህ ደስ ይለኛል (አዎ)
ደስ ይለኛል (እሰይ) ደስ ይለኛል (አዎ)

ስጠራህ ወዳጄ (አሃ)
ከተፍ ትላለህ (እህ)
ቀንበሬን ሰባብረህ (እህ)
ታሳርፈኛለህ (አዎ)
ደስ ይለኛል (አዎ)

ጠላት ሲከበኝ ሲያስፈራራኝ
ተስፋ ማደርገው ሲጠፋብኝ
ድቅድቅ ጨለማ ዙሪያዬ ከቦኝ
እማየው ሁሉ ሙትኝ ሲመስለኝ
በጭንቄ ሰዓት ደረስክልኝ (አዎ)
ጨለማዬንም ገፈፍክልኝ (እሰይ)
እጅግ ደስ አለኝ በማዳንህ
ነፍሴ ሁልጊዜ አንተን ትባርክህ
አንተን ትባርክህ የእኔ ጌታ
አንተን ትባርክህ (አዎ)

አዝ እኔስ በአንተ ጌታ ደስ ይለኛል አዎ
ደስ ይለኛል (እሰይ) ደስ ይለኛል (አዎ)
ጌታ በማዳንህ ደስ ይለኛል (አዎ)
ደስ ይለኛል (እሰይ) ደስ ይለኛል (አዎ)

ስጠራህ ወዳጄ (አሃ)
ከተፍ ትላለህ (እህ)
ቀንበሬን ሰባብረህ (እህ)
ታሳርፈኛለህ (አዎ)
ደስ ይለኛል (አዎ)

በምህረትህና በቸርነትህ ዓመታቶችን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውም ስምህን ይጠግባል
በበረት ውሃም ይጥለቀለቃል
መንጐችህ ሁሉ ይደሰታሉ
የአንተን ማዳን ያኔ ያያሉ
አንዴት ደስ ያሰኛል አቤቱ ስራህ
አንተ ለሕዝብህ መልካም አምላክ ነህ
መልካም አምላክ ነህ የእኔ ጌታ
መልካም አምላክ ነህ (አዎ)

አዝ እኔስ በአንተ ጌታ ደስ ይለኛል አዎ
ደስ ይለኛል (እሰይ) ደስ ይለኛል (አዎ)
ጌታ በማዳንህ ደስ ይለኛል (አዎ)
ደስ ይለኛል (እሰይ) ደስ ይለኛል (አዎ)

ስጠራህ ወዳጄ (አሃ)
ከተፍ ትላለህ (እህ)
ቀንበሬን ሰባብረህ (እህ)
ታሳርፈኛለህ (አዎ)
ደስ ይለኛል (አዎ)