አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (Abietu Endante Manew) - ዮሴፍ ፡ በቀለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሴፍ ፡ በቀለ
(Yosef Bekele)

Yosef Bekele 1.jpg


(1)

ባለውለታዬ ፡ ጌታ
(Baleweletayie Gieta)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ በቀለ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Bekele)

ዙሪያዬ ፡ ሲጨልምብኝ ፡ መሄጃው ፡ ግራ ፡ ሲገባኝ
ዓይኖቼን ፡ ወዳንተ ፡ አቀናሁ ፡ ረዳቴን ፡ ፍጠንልኝ ፡ አልኩኝ
አንተም ፡ አንጊዳጐድክና ፡ ጠላቴንም ፡ በተንክና
ዳግም ፡ አጽንተህ ፡ አቆምከኝ ፡ ብርቱ ፡ ጦረኛም ፡ አረከኝ

አዝ፦ በሃዘን ፡ ችግሬ ፡ ጊዜ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ደራሽ ፡ አጋዤ
ስጠራህ ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስ ፡ ሳነባ ፡ እምባዬን ፡ ምታብስ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ አባባ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኢየሱሴ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው

ጠላቴ ፡ ወጥመድ ፡ ዘርግቶ ፡ በብርቱ ፡ ነፍሴን ፡ ፈልጐ
ዙሪያዬን ፡ ሲዞር ፡ ሲያደባ ፡ ሲዶልት ፡ ከእጁ ፡ ሊያስገባ
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻድቅ ፡ ነህ ፡ በቅን ፡ የምትፈርድ
ወጥመዱን ፡ ሰባበርክልኝ ፡ ከለላ ፡ እምባዬ ፡ ሆንክልኝ

አዝ፦ በሃዘን ፡ ችግሬ ፡ ጊዜ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ደራሽ ፡ አጋዤ
ስጠራህ ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስ ፡ ሳነባ ፡ እምባዬን ፡ ምታብስ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ አባባ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኢየሱሴ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው

በምክርህ ፡ አንተ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ሁሉን ፡ በፍቅር ፡ የያዝህ
ምሬቴን ፡ ከእኔ ፡ አውጥተሃል ፡ በፍቅር ፡ ቃል ፡ አጽናንተኸኛል
የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ ያበራህ ፡ ቅጥቅጥ ፡ ሸምበቆዬን ፡ ያጸናህ
እንዳንተ ፡ ማን ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ልክፈል ፡ ለአንተስ ፡ ውለታ

አዝ፦ በሃዘን ፡ ችግሬ ፡ ጊዜ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ደራሽ ፡ አጋዤ
ስጠራህ ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስ ፡ ሳነባ ፡ እምባዬን ፡ ምታብስ
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ አባባ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ኢየሱሴ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው

እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ማን
እንዳንተ ፡ ማነው ፡ አባባ ፡ ኢየሱስ
እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ማን
እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ለእኔ ፡ የደረሰው

አንተን ፡ ብዬ ፡ ስምህን ፡ ጠርቼ
መቼ ፡ አፍሬ ፡ አውቃለሁ
ጌታ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ጧት ፡ ማታ

አመልክሃለሁ (፬x)
አመልክሃለሁ (፬x)