Tensefsife (Tensefsife) - Yosef Aschalew

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Yosef Aschalew
(Yosef Aschalew)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(Tensefsife)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 6:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የYosef Aschalew ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Aschalew)

እድል ከሰጠኸኝ እንዳገለግልህ
ከአዕላፋት መሃል እኔ ከታየውህ
ልጅህን በእኔ ሁኔታ ከገለጥክ
ፊትህ እንዳጥንልህ ጌታ አንተ ከወደድክ

ተንሰፍስፌ ነው ማገለግልህ
ተንሰፍስፌ ነው ምዘምርልህ
ተንሰፍስፌ ነው ላንተ ምኖረው
ተንሰፍስፌ ነው እድል ካገኘው

እንደ ሺህ አመት ነዋሪ አልንደላቀቅም
ጸጋን ስትሰጠኝ ግዜን አልነሳህም
አፍታ እንደቀረው ሰው ጉድ ጉድ እላለው
አገልግለኝ ካልከኝ እድሉን ካገኘው

ቃል የገባውትን ያኔ በለጋነት
ገና ቅኔ ሳይፈልቅ ከእኔ አንደበት
ላጥፈው አልፈልግም ላንተ ያለኝን ቦታ
ጭብጨባው ሲበዛ ከፍ ከፍ ያልኩ ለታ
             ከፍ ከፍ ያልኩ ለታ
       ነገን እንደሚሞት የዛሬን ቀን ኖሮ
       ማታ እንደማይቆይ ከጠዋት ዘምሮ
       እንሰፈሰፋለው እንደሚያመልጠው ሰው
       አፍታ አይጉደልብህ እኔ ከምኖረው
                 በምድር ከምኖረው

ከአዕላፍ ሰዓታት ከማሳልፋቸው
ከቀናቶቼም ውስጥ ከምኖርባቸው
ከዘመኔም፡መሃል ምርጡን እድሜ አይቼ
ላንተ ሰጥሃለው ቆንጆውን ለይቼ
            ጎበዙን ለይቼ
ብዙ ግዜ አቅርቤ ጭብጨባና እልልታ
ውስጤ አልረካ አለኝ ብሰጥህ የኔ ጌታ
ዛሬ ግን እድሜዬን ፊትህ አቀርበዋለው
ላንተ ማቃጥለው መስዋዕቴ ይህ ነው
        ማርድልህ እድሜዬን ነው