Yohannes Girma/Talking Songs/Yezemenih Bizat

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘመናት ሳይፈጠሩ አንተ አለህ
አንድም የሚታይ በስፍራው ሳይኖር ኖረህ ታውቃለህ
ሁሉ ካንተ ደግሞም ባንተ ላንተ ሆኗልና
ተመልሶ ይልሃል ምስጋና

አቤት የዘመንህ ብዛት
አቤት የክብርህ ብዛት
አቤት የምሕረትህ ብዛት
አቤት አቤት አቤት

በዕድሜ ዘመናችን ሁሉ እናመልክሃለን
ከዚህስ ሌላ ምን አማራጭ አለን
ክብርህ በዝቶ አንበርክኮናል
ወድቀን ሰግደን ልናመልክህ በፊትህ ሆነናል

አቤት የዘመንህ ብዛት
አቤት የክብርህ ብዛት
አቤት የምሕረትህ ብዛት
አቤት አቤት አቤት

የውበትና የመስሕብህ ምንጭ የልቀት ፍጻሜ
ስትማርክ መሊኪያ የለህ አንተ
በምን ቋንቋ በየቱ አንደበት ገድልህን እናውራ
ተደነቅንብህ ቃል አንድ እስኪጠፋ