From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አያለሁ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን
በታላቅ ክብር ተንሰራፍቶ ያለውን
ሁሉን የሚገዛውን እግዚአብሄር
አያለሁ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን
የነበረ ያለ ደግሞ ሚኖረውን
ሁሉን የሚችለውን እግዚአብሄር አያለሁ
አምላኬ የነበረ ያለ ደግሞም የሚኖር ለዘለዓለም
ብቻውን አምላክ ሌላ የሌለህ ሚስተካከልህ
በሰማያት ተንሰራፍቶ ያለ ሃሌሉያ
ግሩም ነው ድንቅ ነው/4
አቤት አቤት አቤት
አቤት ውበት የአምላኬ
መቅደሱን የሞላው ክብርና ግርማው
ዘምር ዘምር ይላል
ክብር ሳትቆጥብ አብዝተህ ስጥ ይላል
አያለሁ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን
በታላቅ ክብር ተንሰራፍቶ ያለውን
ሁሉን የሚገዛውን እግዚአብሄር
አያለሁ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን
የነበረ ያለ ደግሞ ሚኖረውን
ሁሉን የሚችለውን እግዚአብሄር አያለሁ
እልፍና አላእፍት መላእክት
በመንቀጥቀጥ የሚሰግዱለት
ኪሩቤል ሱራፌል ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሚሉት
በሰማያት ተንሰራፍቶ ያለ ሃሌሉያ
ግሩም ነው ድንቅ ነው/4
አቤት አቤት አቤት
አቤት ውበት የአምላኬ/2
መቅደሱን የሞላው ክብርና ግርማው
ዘምር ዘምር ይላል
ክብር ሳትቆጥብ አብዝተህ ስጥ ይላል/2
አቤቱ አንተ ከምናውቅህ በላይ ነህ
ስላተ የነገሩን ካስታወቁን በላይ እጅግ ጥልቀት አለህ
አቤቱ አንተ ከምናውቅህ በላይ ነህ
ስላንተ የሰበኩን ካስታወቁን በላይ እጅግ ጥልቀት አለህ
ጥበብህ ማይመረመር
ማስተዋልህ ማይለካ
የሃይልህ ብዛት አይመዘን
የዘላለም አምላክ
ግልበት ሁሉ ሊንበረከክ
ክብርን ሊሰጥ የተገባህ የተገባህ
ምላስ ሁሉ ጌትነትህን
ሊመሰክር የተገባህ የተገባህ
|