እርስቴ ፡ ነህ (Erestie Neh) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 2.jpg


(2)

እርስቴ ፡ ነህ
(Erestie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:39
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

አንተ ፡ ላወቁብህ ፡ ክብር ፡ ነህ
የማዕረግ ፡ መጐናፀፊያ
የሃዘኑ ፡ ዘመን ፡ ማስረሻ
ከማይነጥፍ ፡ ሰላም ፡ መድረሻ

በዕረፍት ፡ ወንዝ ፡ ዳር ፡ ይተከላል
ያገኘህ ፡ ከምንጭ ፡ ዳር ፡ ይኖራል
ዕርዳታው ፡ ከሰማይ ፡ ደጅ
ይወርዳል ፡ የእግዚአብሔር/የአምላኩ ፡ እጅ (፪x)

አዝ፦ እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ
ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ
ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ
ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ (፪x)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ ማይገኝ
ቢተካስ ፡ በሌላ ፡ ማያሰኝ
መኖሪያህ ፡ በብርሃናት ፡ ውስጥ
ውበት ፡ ነህ ፡ ለርስትህ ፡ ጌጥ

ለዘለዓለም ፡ ትኖራለህ
ማያረጁ ፡ ዓመታት ፡ ይዘህ
ለሁሌ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ/የእኔ ፡ ምርጫ
ከአዕላፋት ፡ አግኝተህ ፡ ብልጫ (፪x)

አዝ፦ እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ
ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ
ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ
ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ (፪x)

ለሰማይ ፡ ዉበትን ፡ የሰጠህ
ለምድር ፡ ዳርቻን ፡ ያበጀህ
እኔን ፡ በአምሳልህ ፡ መፍጠርህ
የከበርሁ ፡ አርገህ ፡ ማየትህ

ልቤ ፡ በመደነቅ ፡ ተሞላ
ክብሬ ፡ ሊያዜምልህ ፡ ተነሳ
ከልብ ፡ የሚፈልቅ ፡ ምሥጋና
መስዋዕቴ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይግባ (፪x)

አዝ፦ እርስቴ ፡ ነህ ፡ የልቤ ፡ ምርጫ
ነፍሴ ፡ አፀደቀህ ፡ የፈቃዴ ፡ ብልጫ
ሁሉንም ፡ ንቄያለሁ ፡ ክብር ፡ በፊቴ ፡ አጣ
ሁሉን ፡ ጥሎ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሃሳብህ ፡ መጣ
ጌታ ፡ ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ እያየለ ፡ መጣ (፪x)