የመውደዴ (Yemewdedie) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 3.jpg


(3)

አምላኬ ፡ ደስታዬ
(Amlakie Destayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

የመውደዴን ፡ ብዛት ፡ የፍቅሬንም ፡ ብዛት
በውስጤ ፡ ያለውን ፡ የንዳዱን ፡ ብርታት
የማረከኝን ፡ የተረታሁልህን
ልገልጠው ፡ አልችልም ፡ አንተ ፡ ያረክልኝን (፪x)

አሸንፈኸኛል ፡ እመሰክራለሁ
ጌታ ፡ አፌን ፡ ሞልቼ ፡ እናገራለሁ (፪x)

የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ውስጤ ፡ ያለው
እየጨመረ ፡ የሚሄድ ፡ ወንዝ ፡ ነው
አሁንስ ፡ ሳየሁ ፡ ይህ ፡ ገብቶኛል
የማልወጣው ፡ ነገር ፡ ይዞኛል (፫x)

የምልህ ፡ አለኝ ፡ የምልህ
ቋንቋን ፡ አጥቼ ፡ ያኖርኩልህ
ቃላት ፡ አግኝቼ ፡ መጥቻለሁ
ኢየሱስዬ ፡ ወድሃለሁ (፪x)

ኧረ ፡ ማን ፡ ሊተካህ ፡ አንተን (፪x)
ስፍራህን ፡ የሚወስድ ፡ ከወዴት ፡ ሊገኝ
በሰማይ ፡ የለም ፡ በምድርም ፡ የለም
ከምድርም ፡ በታች ፡ አይገኝ (፪x)