From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
መቅበዝበዝ ሳበዛ በዓለም ስዋትት
ክብር መስሎኝ ታይቶኝ ውርደት ሳካብት
በበደሌ ብዛት ሞት የሚገባኝን
ፀጋህን አብዝተህ በህይወት ኖርኩኝ
ዛሬ ላንተ ቆሜ ባፌ ዘምራለሁ
ያዳንከውን አዳዳን ገድልህን አወራለሁ
ግነን በዓለማት ስምህ ከፍ ይበል
በእርግጥ ከዚህ በቀር የለም የምከፍልህ
አንተን ያገኘሁ ለት መንገዴ ተቃና
በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና
ፍቅርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል
ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያፀድቃል (2)
ስንከራተት ሳለ በምድረበዳ ላይ
የሚረዳኝ የለም ግራ ቀኜን አላይ
ባልጠበኩት ለታ ከሰማይ ድምፅ መጣ
በእጁ እጄን ያዘኝ ተራራን አወጣኝ
አንተ የኔ እኮ ነህ ልጄ እወድሃለሁ
በእውነት ቃል አስቤህ ለክብር ወልጄሃለሁ
ለዘላለም ፍቅሬ ካንተ አትለይም
አለኝ ለዘለዓለም እኔ አልጥልህም
አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ)
እርጥበት የማያውቅ በድርቅ የደቀቀ
ህይወቴ ነበረ ከአጥንት የደረቀ
ከፍጥረቴ ሳለሁ የበረሃ ወይራ
መጠጊያን አገኘሁ በመልካሙ ስፍራ
ኩሩው ሊያስቀና ምስኪኑን መረጠ
ከውድረደት አንስቶ ለክብር አስቀመጠ
በእርሱ ተተክዬ በመልካሙ ግንድ ስር
ልምላሜን አገኘሁ ለዘላለም ይክበር
አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ)
ጠመዝማዛ ጉዞ ቁልቁለት ሳዘግም
ሞቴን ለማፋጠን ኃጥያትን ስቃርም
በጠላት ድለላ በእርሱ ጦር ታጅቤ
ከፍቅር አባቴ ካንተ ሲሸሽ ልቤ
እንደ ህጻን አርገህ በእርጋታ መከርከኝ
ሳላውቅ እንዳልጠፋ ፍቅርህ ሰበሰበኝ
አንተ ካስጠጋኸኝ የሚከሰኝ ማነው
ነፃ ያወጠኸኝ ከልብህ ወደህ ነው
አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ)
|