Yohannes Girma/Amlakie Destayie/Lekebreh Yemihon Eqa

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ጨለማ በሆነበት ብርሃንን የሚያበራ ስለ ከበረው ፀዳልህ ሚያወራ ሙት በገዛው ሸለቆ ሕይወትን የሚናገር ወደ ሞት ለሚነዱት ብርሃን የሚሆን የምሥራችን የሚያበስር

   ለክብርህ የሚሆን እቃ (3 ጊዜ)
   አርገኝ ጌታ
   ለክብርህ የማያሳፍር
   ክቡር ስምህን የሚሸከም

ሙሉ ማንነቱን ላንተ የሚሰጥ ታማኝ ባርያ የማያሳፈር (2 ጊዜ)


የወርቅ እቃ መጥነህ በእሳትህ የነጠረ የምትሻውን ልታደርግበት ያማረ ሕያው ቅዱስ መስዋዕት አርጎ ራሱን የሰጠ ባለህበት አብሮ የሚኖር የማይለቅ እንዳስቀመጥከው የሚቀመጥ

   ለክብርህ የሚሆን እቃ . . .

በዓለም ከሚታይ በደል ከጊዜያዊ ደስታ ሰማያዊውን ለመያዝ ልዘርጋ ዓለምን ነፍሴ ትጥላ በአይኖቼ ክብርን ትጣ በርቀት እያየኋት ላንት ልሩጥ ፍሬን ላፍራ አንትን ላኩራ

   ለክብርህ የሚሆን እቃ . . .