ከጠዋት ፡ አንስቶ (Ketewat Anseto) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 3.jpg


(3)

አምላኬ ፡ ደስታዬ
(Amlakie Destayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 7:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

አቅም ፡ ስጠኝና ፡ አብዝቼ ፡ ልውደድህ
መቼም ፡ ልጥገብህ ፡ አልል ፡ አንተ ፡ አትጠገብም
ሰው ፡ ቢያንገራግር ፡ እስከሚገባው ፡ ነው
የበራለት ፡ ለታ ፡ ለመውጣት ፡ የሚያስቸግር
ፍቅርህ ፡ እጅግ ፡ ብርቱ ፡ ነው

አዝ፦ ከጠዋት ፡ አንስቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ ድረስ
ከምሽት ፡ አንስቶ ፡ እስከ ፡ ንጋት ፡ ድረስ
ብትወደድ ፡ አትጠገብም (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ፡ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ

ላልወድህ ፡ አልችልም ፡ ላልቀርብህ ፡ አብዝቼ
የተገኘሁብህ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ምንጬ
እጅግ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ያለን ፡ ትስስር
ከጥንት ፡ የነበረ ፡ ዛሬም ፡ ያለ ፡ ለዘለአለም
የሚቀጥል ፡ ነገር

አዝ፦ ከጠዋት ፡ አንስቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ ድረስ
ከምሽት ፡ አንስቶ ፡ እስከ ፡ ንጋት ፡ ድረስ
ብትወደድ ፡ አትጠገብም (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ፡ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ

ከጥንት ፡ ከማለዳ ፡ የኔ ፡ ያንተ ፡ ነገር
ማቆምያም ፡ የለውም ፡ ጊዜያትን ፡ ሲሻገር
ሁሉ ፡ ነገር ፡ ያልፋል ፡ አንድ ፡ ሳይቀር ፡ ጠፊ ፡ ነው
ለኔ ፡ ያለህ ፡ ነገር ፡ እኔም ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ነገር
ዘለዓለም ፡ ኗሪ ፡ ነው

አዝ፦ ከጠዋት ፡ አንስቶ ፡ እስከሚመሽ ፡ ድረስ
ከምሽት ፡ አንስቶ ፡ እስከ ፡ ንጋት ፡ ድረስ
ብትወደድ ፡ አትጠገብም (፫x) ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ፡ ጌታ
እወድሀለሁ (፫x) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ