Yohannes Girma/Amlakie Destayie/Kemegegneteh Wediet Ehiedalehu

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ዮሐንስ ግርማ ሌላ ሥም ጆኒ ርዕስ ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ አልበም አምላኬ ደስታዬ

ከአፈር የተነቀለ ሳር ጠውልጐ ደርቆ እንደሚታይ ልምላሜን ርቆ ከሕልውናህ ውጭ መኖር ለእኔ ይከብዳል ክፍት ክፍት እያለ ሁሌ ሆድ ያስብሳል (፪x)

አዝ ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (፪x)

በእጆችህ አጥብቀህ እኔን ይዘኸኛል ይህንንም እውነት ቃልህ ይናገራል ነገሩ ከገባኝ ዕንቁ መሆንህ ለምን አንተ ብቻ እኔም ልያዝህ/ላጥብቅህ (፪x)

አዝ ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (፪x)

ከአንተ እርቆ ሰው እንዴት እንደሚኖር እኔ አይገባኝም ትምክህቱ ምን ይሆን ከህልውናህ ውጭ እልፍ ከሚያጅበኝ ከመገኘትህ ውስጥ የተጣልኩ ያድርገኝ (፪x)

አዝ ከመገኘትህ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (፪x)