ሃሌሉያ (Hallelujah) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 3.jpg


(3)

አምላኬ ፡ ደስታዬ
(Amlakie Destayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 7:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

በምድር ፡ ላይ ፡ ብዙዎች ፡ አማልክቶች ፡ ይኖራሉ
እያንዳንዳቸው ፡ በሚያመልኳቸው ፡ ይበጃሉ/ይሰራሉ (፪x)
ብቻውን ፡ የእኔ ፡ ምሥጋና ፡ የተገባ
ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ከእርሱና ፡ ለእርሱ ፡ የሆነው
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝሃሌሉያ (፰x)
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር

እርሱ ፡ ፈጥሮ ፡ ሕያው ፡ እስትንፋስ ፡ የሰጣችሁ
የእጁ ፡ ሥራዎች ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ያላችሁ (፪x)
ድምጻችሁን ፡ ከፍ ፡ አድርጋችሁ ፡ በምሥጋና
የሚገባውን ፡ ክብር ፡ ያግኝና
ይክበር ፡ በምሥጋና

አዝሃሌሉያ (፰x)
ክብር ፡ ለእግዚአብሔር

የሰው ፡ ዘሮች ፡ በየአገራቱ ፡ ያላችሁ
ልዩ ፡ ቀለም ፡ ልዩ ፡ ልዩ ፡ ሕዝቦች ፡ በቋንቋችሁ (፪x)
ለሥሙ ፡ የሚገባውን ፡ ክብር ፡ አምጡ
በቅድስናው ፡ ሥፍራ ፡ ስገዱ
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ በሉ

ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ (ክብሩ) ፡ ነው (፫x)
. (1) . ፡ አምላክ ፡ ለሆንከው
ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)