አንተ ፡ ዘለዓለም ፡ ነህ (Ante Zelalem Neh) - ዮሐንስ ፡ ግርማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ ግርማ
(Yohannes Girma)

Yohannes Girma 3.jpg


(3)

አምላኬ ፡ ደስታዬ
(Amlakie Destayie)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ ግርማ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Girma)

የምድር ፡ ዳርቻዎች ፡ ፈጣሪ
ውሆችን ፡ በእፍኝህ ፡ የሰፈርህ
ሰማየ ፡ ሰማያት ፡ የአንተ ፡ ናቸው
በግርማዊነትህ ፡ ሰራሃቸው
ጥንት ፡ የነበርህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ
ለዘለአለም ፡ የምትኖር (፪x)

አዝአንተ ፡ ዘለአለም ፡ ነህ (፪x)
ጅማሬና ፡ ፍጻሜ ፡ የሌለህ
ጌታ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x)

ሰማይና ፡ ምድር ፡ በስፍራቸው
ሳይኖሩ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ቀድመሃቸው
ጅማሬ ፡ የለህም ፡ ፍጻሜ
እድሜህ ፡ አይሰላ ፡ ሰው ፡ አይደለህ
ጥንት ፡ የነበርህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ
ለዘለአለም ፡ የምትኖር (፪x)

አዝአንተ ፡ ዘለአለም ፡ ነህ (፪x)
ጅማሬና ፡ ፍጻሜ ፡ የሌለህ
ጌታ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፪x)

ከአማልክት ፡ መሃከል ፡ እንደአንተ ፡ ማን ፡ ነው
የእኔን ፡ ጌታ ፡ እግዚኣብሔር ፡ የሚመስለው
አምላኬ ፡ ከሁሉም ፡ ትለያለህ
አንተ ፡ የአማልክት ፡ ሁሉ ፡ አምላክ ፡ ነህ
ጥንት ፡ የነበርህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ
ለዘለአለም ፡ የምትኖር (፪x)

አዝአንተ ፡ ዘለአለም ፡ ነህ (፪x)
ጅማሬና ፡ ፍጻሜ ፡ የሌለህ
ጌታ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ (፬x)