Yohannes Girma/Amlakie Destayie/Amlakie Destayie
ከቶውን በለስ ባያፍራ በወይንም ሐረግ ላይ ፍሬ ባይገኝ የወይራ ሥራ ቢጐድል እርሾችም መብልን ባይሰጡ
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሃሴት አደርጋለሁ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያበረታል በከፍታዎች ላይ ያስኬደኛል (፪x)
አምላኬ ደስታዬ ደስታዬ ነህ ኢየሱሴ ሙላቴ እርካታዬ ነህ (፪x)
በቅተኸኛል ሌላም አልፈልግም ቀረም የምለው ነገርም የለኝ ታምኜብህ በሁሉ ነገሬ ይዤ መጣሁ የከንፈሬን ፍሬ (፪x)
ምን ይከብደው ብዬ ለየትኛው ልፍራ ምን ያቅተውና ምኑን ብዬ ልፍራ (፪x)
ተራራ ላይ ማዳን የቻለው ሸለቆው ውስጥ ኃይል የእርሱ ነው ሁሉን ሚችል ሥሙ ኤልሻዳይ የእኔ አምላክ ያለ በሰማይ (፪x)
እንደ እግዚአብሔር ያለ ከወዴት ይገኛል የሕዝቡ መከታ ፅኑ ጋሻ ሆኗል (፪x)
መመኪያ ነው ለትውልድ ትምክህት መጓደጃ የልጅ ልጅ ኩራት ሚታመኑት ከፍ ከፍ ይላሉ ለዘለዓለም ማዳኑን ያያሉ
ከቶውን በለስ ባያፍራ ከወይንም ሃረግ ላይ ፍሬ ባይገኝ የወይራ ሥራ ቢጐድል እርሾችም መብልን ባይሰጡ
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሃሴት አደርጋለሁ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ፡ ያበረታ በከፍታዎች ላይ ያስኬደኛል (፪x)