ይሁን ፡ ሆይ (Yehun Hoy) - ዮሐንስ ፡ በላይ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay)

Yohannes Belay 3.jpg


(3)

ጽድቁን
(Tsedqun)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

አዝይሁን ፡ ሆይ (፪x)
ፈቃድህን ፡ ልጠይቅ ፡ ይሁን ፡ ሆይ
የእኔ ፡ መንገድ ፡ የሚያምረው
አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ስትመራኝ ፡ ነው (፪x)

አንተ ፡ የሌለህበት ፡ ብራብ ፡ ላያጠግበኝ
መንገዴም ፡ ላይቀና ፡ ሕይወት ፡ ላይሆንልኝ
ልጠይቅ ፡ ፈቃድህን ፡ አባቴ ፡ ነህና
እሾህ ፡ ማይኖረው ፡ መንገዴ ፡ ሲቀና (፪x)

አሃሃ ፡ በጐ ፡ መስሎኝ ፤ አሃሃ ፡ በዓይኔ ፡ አይቼ
አሃሃ ፡ ተጐዳሁኝ ፤ አሃሃ ፡ ውስጥ ፡ ገብቼ
አሃሃ ፡ ያየህልኝን ፤ አሃሃ ፡ እንድወርሰው
አሃሃ ፡ ምራኝ ፡ ጌታ ፤ አሃሃ ፡ እንድደርሰው (፪x)

አዝይሁን ፡ ሆይ (፪x)
ፈቃድህን ፡ ልጠይቅ ፡ ይሁን ፡ ሆይ
የእኔ ፡ መንገድ ፡ የሚያምረው
አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ስትመራኝ ፡ ነው (፪x)

በሕይወቴ ፡ ስጓዝ ፡ ባለፉት ፡ ዘመናት
ራሴን ፡ ሰምቼ ፡ ወጣሁኝ ፡ ለጥፋት
ያኔ ፡ ይበቃኛል ፡ የሳትኩት ፡ መንገዴ
ምራኝ ፡ እንደቃልህ ፡ በአንተ ፡ ይሁን ፡ ውዴ (፪x)

አሃሃ ፡ በጐ ፡ መስሎኝ ፤ አሃሃ ፡ በዓይኔ ፡ አይቼ
አሃሃ ፡ ተጐዳሁኝ ፤ አሃሃ ፡ ውስጥ ፡ ገብቼ
አሃሃ ፡ ያየህልኝን ፤ አሃሃ ፡ እንድወርሰው
አሃሃ ፡ ምራኝ ፡ ጌታ ፤ አሃሃ ፡ እንድደርሰው (፪x)

አዝ፦ የእኔ ፡ መንገድ ፡ የሚያምረው
አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ጌታዬ ፡ ስትመራኝ ፡ ነው
ይሁን ፡ ሆይ (፪x)
ፈቃድህን ፡ ልጠይቅ ፡ ይሁን ፡ ሆይ
የእኔ ፡ መንገድ ፡ የሚያምረው
አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ስትመራኝ ፡ ነው