From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የምድረበዳ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ (አሃሃ) ፡ ሁሉን ፡ ያለፍኩብህ
የምድረበዳ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ (አሃሃ) ፡ ሁሉን ፡ ያረሳሁብህ
ኧረ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x)
እኔ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም
ኧረ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x)
እኔ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x)
ዓሣ ፡ ከውኃ ፡ ውጭ ፡ እንደማይኖር ፡ እስትንፋስ ፡ ፡ ርቆት
ሕይወቴም ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ የሌለህበት
ሸካራው ፡ መንገዴን ፡ አለስልሰህ ፡ በፍቅር ፡ ይዘኸኝ
ጥልቅህ ፡ ፍቅርህ ፡ ይዞ ፡ እየመራኝ ፡ በሕይወት ፡ አኖረኝ
አስፈሪውን ፡ መንገድ ፡ ሆነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በእጆችህ ፡ ይዘኸኝ ፡ እንዴት ፡ ልቤ ፡ ይፍራ (፪x)
ሲከፋኝ ፡ ስጨነቅ ፡ አጠገቤ ፡ ነህ ፡ ግራ ፡ ሲገባኝ
ከጐኔ ፡ ምትቆም ፡ ሳትሰለቸኝ ፡ ምታበረታኝ
የልጅነቴ ፡ አምላክ ፡ ምትሸከመኝ ፡ ከነማንነቴ
የሕይወት ፡ ማብቂያ ፡ ነህ ፡ መደምደሚያዬ ፡ የመጨረሻዬ
አስከፊውን ፡ መንገድ ፡ ሆነህ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በእጆችህ ፡ ይዘኸኝ ፡ እንዴት ፡ ልቤ ፡ ይፍራ (፪x)
የምድረበዳ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ (አሃሃ) ፡ ሁሉን ፡ ያለፍኩብህ
የምድረበዳ ፡ ወዳጄ ፡ ነህ (አሃሃ) ፡ ሁሉን ፡ ያረሳሁብህ
ኧረ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x)
እኔ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም
ኧረ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x)
እኔ ፡ ያለአንተ ፡ አልኖርም (፪x)
|