From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አምላኬን ፡ ልፈልግ ፡ በጠዋት ፡ በማታ (፪x)
ጽድቁን ፡ ብቻ ፡ ልራብ ፡ መሽቶም ፡ እስኪነጋ (፪x)
አምላኬን ፡ ልፈልግ ፡ በጠዋት ፡ በማታ (፪x)
ጽድቁን ፡ ብቻ ፡ ልራብ ፡ መሽቶም ፡ እስኪነጋ (፪x)
ጽድቁን ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ እራቤ
ጽድቁን ፡ ነው ፡ ነገም ፡ ጥማቴ
ጽድቁን ፡ ነው ፡ ሁሌም/ዛሬም ፡ እረሃቤ
የምድሩ ፡ ትርፍ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)
በጉብዝናህ ፡ ወራት ፡ ፈጣሪን ፡ ማሰብ
ይሻል ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር
ይሄ ፡ ሚስጥር ፡ ገብቶኝ ፡ የምድሩን ፡ ንቄያለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እኔስ ፡ እጠግባለሁ
በጉብዝናህ ፡ ወራት ፡ ፈጣሪን ፡ ማሰብ
ይሻል ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር
ይሄ ፡ ሚስጥር ፡ ገብቶኝ ፡ የምድሩን ፡ ንቄያለሁ
ጽድቁን ፡ ብቻ ፡ ሳስብ ፡ እኔስ ፡ እጠግባለሁ
አይበልጥም ፡ ወይ (፬x) ፡ ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
አይበልጥም ፡ ወይ (፬x) ፡ ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
ስለምድር ፡ ሳስብ ፡ ለሚያልፈው ፡ ስጨነቅ
ዓመታት ፡ አለፉ ፡ ብዙ ፡ ለፋሁ ፡ ደከምኩ
አሁን ፡ በልጦብኛል ፡ የላዩ ፡ ተስፋዬ
አይረባኝም ፡ አወቅኩ ፡ የምድሩን ፡ መቆፈሬ (፪x)
አይበልጥም ፡ ወይ (፬x) ፡ ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
አይበልጥም ፡ ወይ (፬x) ፡ ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
አይበልጥም ፡ ወይ (፬x) ፡ ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
አይበልጥም ፡ ወይ (፬x) ፡ ጌታ ፡ አይሻልም ፡ ወይ
|