From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ዮሐንስ ፡ በላይ (Yohannes Belay)
|
|
፫ (3)
|
ጽድቁን (Tsedqun)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፮ (2014)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፩ (11)
|
ርዝመት (Len.):
|
6:01
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች (Albums by Yohannes Belay)
|
|
ከልብ ፡ የሆነ ፡ ምሥጋናዬን
ልሰዋ ፡ በፊትህ ፡ ጌታዬ
ከልብ ፡ የሆነ ፡ አምልኮዬን
ልሰዋ ፡ በፊትህ ፡ ጌታዬ
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋናዬን
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮዬን
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋናዬን
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮዬን
ልሰዋ ፡ ምሥጋናዬን ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮዬን (፪x)
ሁኔታን ፡ አይቼ ፡ በገና ፡ አላነሳም
ሞላ ፡ አልሞላም ፡ ብዪ ፡ አምልኮ ፡ አልቀንስም
የለት ፡ ነው ፡ ተግባሬ ፡ ስምህን ፡ ማወደስ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ስትከብር ፡ ይለኛል ፡ ደስ ፡ ደስ (፪x)
ምሥጋናን ፡ ሚሰዋ ፡ ስምህን ፡ ያከብረዋል
ማዳንህን ፡ ደግሞ ፡ በምሥጋናው ፡ ያወራል (፪x)
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋናዬን
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮዬን
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ ይዘሃል
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ተቀምጠሃል
ፍጥረት ፡ ይስገድልህ ፡ ፍጥረት ፡ ያመስግንህ
መላዕክት ፡ ለስምህ ፡ ለክብርህ ፡ ይስገዱልህ (፪x)
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋናዬን
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮዬን
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ ምሥጋናዬን
ልሰዋልህ (፪x) ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮዬን
ልሰዋ ፡ ምሥጋናዬን ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮዬን (፪x)
|