የሚመካ (Yemimka) - ዮሐንስ ፡ በላይ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay)

Lyrics.jpg


(4)

ላድንቅህ
(Ladenekeh)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ላይ ፡ የሚታመን
የተረገመ ፡ ነው ፡ እንደሚለው ፡ ቃሉ
በኢየሱስ ፡ ሚታመን ፡ አያፍርም ፡ አያፍርም ፡ ይላል ፡ ቃሉ

አንተን ፡ ተከትሎ ፡ የዳነ
ሰላሙ ፡ በዝቶለት ፡ እርፍ ፡ አለ
አስተማማኝ ፡ ጥላ ፡ ሆንከው
አይፈራ ፡ ሥጋት ፡ አያውቀው X፪

በጌታ ፡ ሚመካ ፡ ይመካ
በኢየሱስ ፡ ሚደገፍ ፡ ይደገፍ ፡ X፪

አይለዋወጥ ፡ እምነቴ
ጽኑ ፡ ነው ፡ በመድሃኒቴ
ዓይኖቼን ፡ ከሰው ፡ አንስቻለሁ
ቃሉ ፡ ሚለኝን ፡ አምናለሁ ፡ X፪

በጌታ ፡ ሚመካ ፡ ይመካ
በኢየሱስ ፡ ሚደገፍ ፡ ይደገፍ ፡ X፪

ያለኝን ፡ አምናለሁ ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ
ሰው ፡ እንኳን ፡ ተናግሮኝ ፡ ስንቱን ፡ አምኛለሁ
ሚያደርግ ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ሚፈጽም ፡ ፡ ሚተጋ
ጌታን ፡ በማመኔ ፡ አግኝቻለሁ ፡ ዋጋ

በጌታ ፡ ሚመካ ፡ ይመካ
በኢየሱስ ፡ ሚደገፍ ፡ ይደገፍ ፡ X፪