ማን አፈረ (Man Afere) - ዮሐንስ በላይ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ በላይ
(Yohannes Belay)

Lyrics.jpg


(Volume)

ላድንቅህ
(Ladenekeh)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 3:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

እስኪ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ ተማምኖ
ይባርክሃል ፡ እንጂ ፡ ክፉ ፡ ቀኑን ፡ አልፎ
ጭው ፡ ባለ ፡ ለሊት ፡ በሮች ፡ ተዘግተው
ኢየሱሴ ፡ ብሎ ፡ ያልዳነ ፡ ሰው ፡ ማነው

የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ ጩኸትን ፡ የሚሰማ
የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ እንባብ ፡ የሚያይ ፡ ነው
የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ ከምድረበዳ ፡ ላይ
ምንጭ ፡ ያፈልቃል ፡ ያረካል ፡ ደርሶ ፡ ከላይ

ምልክት ፡ ሳይኖት ፡ እድል ፡ ቀዳዳ
በንዳዱ ፡ እሳት ፡ በምድረበዳ
የሚያረሰርስ ፡ አፍልቆ ፡ ውኃ
የሚያለመልም ፡ ደረቅ ፡ በረሃ
አርክተህ ፡ ሁሉን ፡ ታስደንቃለህ
እንዲያው ፡ በመንገድ ፡ መች ፡ ትጥላለህ
የጉብኝት ፡ ቀን ፡ ሰጥተህ ፡ ቀጠሮ
ያልደረስክለት ፡ ማነው ፡ የሚኖር ፡ አፍሮ
ከቶ ፡ አልነበረም ፡ መቼም ፡ አይኖርም
ለተናገርከው ፡ ሳትደርስ ፡ አትቀርም

እስኪ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ ተማምኖ
ይባርክሃል ፡ እንጂ ፡ ክፉ ፡ ቀኑን ፡ አልፎ
ጭው ፡ ባለ ፡ ለሊት ፡ በሮች ፡ ተዘግተው
ኢየሱሴ ፡ ብሎ ፡ ያልዳነ ፡ ሰው ፡ ማነው

የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ ጩኸትን ፡ የሚሰማ
የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ እንባብ ፡ የሚያይ ፡ ነው
የእኔ ፡ እግዚአብሄር ፡ ከምድረበዳ ፡ ላይ
ምንጭ ፡ ያፈልቃል ፡ ያረካል ፡ ደርሶ ፡ ከላይ

ማነው ፡ ጌታውን ፡ ያጣ ፡ ጠብቆ
ባዶ ፡ የቀረ ፡ የእጁን ፡ ተነጥቆ
ተተረከ ፡ እንጂ ፡ አባትነትህ
መች ፡ ተነገረ ፡ ቀጥረህ ፡ መቅረትህ
ጥበብ ፡ አይጎልህ ፡ ታስደንቃለህ
እንዲያው ፡ በመንገድ ፡ መች ፡ ትጥላለህ
የጉብኝት ፡ ቀን ፡ ሰጥተህ ፡ ቀጠሮ
ያልደረስክለት ፡ ማነው ፡ የሚኖር ፡ አፍሮ
ከቶ ፡ አልነበረም ፡ መቼም ፡ አይኖርም
ለተናገርከው ፡ ሳትደርስ ፡ አትቀርም

ማንም ፡ የለም ፡ ያፈረ ፡ አንተን ፡ ተማምኖ
ማንም ፡ የለም ፡ የወደቀ ፡ አንተን ፡ ጠብቆ