ልዩ ነህ (Leyu Neh) - ዮሐንስ በላይ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ በላይ
(Yohannes Belay)

Lyrics.jpg


(Volume)

ላድንቅህ
(Ladenekeh)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

ትላንት ፡ በጆሮዬ ፡ ከሰማሁት
ዓይኔም ፡ አይቶሃል
ልቤም ፡ ወዶሃል
ልዩ ፡ ነሃ
X፪

ልዩ ፡ ነህ ፡ አሃሃ
ፍቅር ፡ ነህ ፡ አሃሃ
ልዩ ፡ አሃሃ
ፍቅር ፡ ነህ ፡ አሃሃ

ወዳጅ ፡ ሸቀጥ ፡ ሆኖ ፡ በገንዘብ ፡ ሲገዛ X፪
ለነገ ፡ ያስቀመጡት ፡ ሲናድ ፡ እንደዋዛ X፪
የእዳ ፡ ጽህፈቴ ፡ በዝቶ ፡ ሲከብደኝ X፪
በደሃ ፡ ጐጆዬ ፡ ገብተህ ፡ አየሁኝ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ አየሁኝ

ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እኮ ፡ ፍቅር ፡ ኧረ ፡ ይለያል
በቀንምም ፡ በማለዳም ፡ ያዘምረኛል
X፪

ልዩ ፡ ነህ ፡ አሃሃ
ፍቅር ፡ ነህ ፡ አሃሃ
ልዩ ፡ አሃሃ
ፍቅር ፡ ነህ ፡ አሃሃ

ለጻድቅ ፡ የሚሞት ፡ በጭንቅ ፡ ተገኝቶ X፪
ሃጢውን ፡ ማን ፡ ይዋስ ፡ ከሰው ፡ መሃል ፡ ወጥቶ X፪
የእዳ ፡ ጽህፈቴ ፡ በዝቶ ፡ ሲከብደኝ X፪
ሕይወትን ፡ ሰጠኸኝ ፡ ቀርበህ ፡ ታደከኝ X፪

ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ የፍቅር ፡ መለኪያህ
እንዲሁ ፡ መወደድህ ፡ ነው ፡ በደምህ ፡ አጥበህ
X፪

ልዩ ፡ ነህ ፡ አሃሃ
ፍቅር ፡ ነህ ፡ አሃሃ
ልዩ ፡ አሃሃ
ፍቅር ፡ ነህ ፡ አሃሃ