አንተን ፡ ተጠማች (Anten Tetemach) - ዮሐንስ ፡ በላይ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay)

Lyrics.jpg


(4)

ላድንቅህ
(Ladenekeh)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

ነፍሴም ፡ እንደ ፡ ውኃ ፡ አንተን ፡ ተጠማች
በቀንም ፡ በማታም ፡ እየናፈቀች (፪x)
ያሰብኩት ፡ ተሳክቶ ፡ እርካታ ፡ ሳይኖረኝ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ሲመጣ ፡ ህይወት ፡ ፈለቀልኝ (፪x)

እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ
የልቤ ፡ ሚገባው ፡ ሌላ ፡ የለምና
ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች
እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ

ደመና ፡ አልባ ፡ ሰማይ ፡ ተንጣሎ ፡ ከፊቴ
ወጀብ ፡ ሲያፏጭባት ፡ ተፋልሳ ፡ ሕይወቴ
በማይቋጭ ፡ ዙሪት ፡ ተስፋ ፡ አጥቼ ፡ ሳለሁ
የዘላለም ፡ ተስፋ ፡ ኢየሱስን ፡ አገኘው
(፪x)

እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ ፡
እርካታ ፡ ሚሞላ ፡ ሌላ ፡ የለምና
ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች
እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ

በልቶም ፡ ይርበዋል ፡ አግኘቶ ፡ ይጐለዋል
ዛሬ ፡ አገኘሁኝ ፡ ሲል ፡ ኪሳራ ፡ ይቀድመዋል
ከምንጩ ፡ የሸሸ ፡ ነፍስ ፡ ከአንተ ፡ ርቆ ፡ የሄደ
የወጣ ፡ ሲመስለው ፡ ወደታች ፡ ወረደ
(፪x)

እኔማ ፡ አላይ ፡ ወደሌላ
እርካታ ፡ ሚሞላ ፡ ሌላ ፡ የለምና
ኑሮዬም ፡ ቢሞላ ፡ ሚመች
እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ስለሆነ ፡ እንጂ

እርካታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እርካታዬ
(፰x)