ረቢ ፡ ሆይ (Rebi Hoy) - ዮሐንስ ፡ በላይ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay)

Yohannes Belay 2.jpg


(2)

ሃሳቤን ፡ ፈውሰው
(Hasaben Fewesew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልማር ፡ ቃልህን
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልወቅ ፡ ቃልህን
ረቢ ፡ ሆይ(፪)

(ረቢ ፡ ሆይ) ፡ ና ፡ አስተምረኝ
(ረቢ ፡ ሆይ) ፡ በቃልህ
(ረቢ ፡ ሆይ) ፡ መንገዴን ፡ አቅና
(ረቢ ፡ ሆይ) ፡ ከሕይወት ፡ ቃልህ(፪)

ቃልህ ፡ ለመንገዴ ፡ ለሕይወቴ ፡ ብርሃን ፡ ነው
ይህን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ የማልፈው ፡ በአንተ ፡ ነው
በሚገባኝ ፡ መንገድ ፡ ና ፡ አስተምረኝ
የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አቅጣጫን ፡ አሳየኝ(፪)

ቃልህ ፡ ይብራልኝ ፡ ጌታ(፪)
እንድኖር ፡ ሁሌ ፡ በእርጋታ
ቃልህ ፡ ይብራልኝ ፡ ጌታ(፪)

ቃልህን ፡ ያገኘ ፡ ልቦናው ፡ ይበራል
ጥበብ ፡ እያበዛ ፡ በክብር ፡ ይዘልቃል
ጥፋት ፡ አያገኘው ፡ ሕይወት ፡ የሚገታ
እርስቱን ፡ ይወርሳል ፡ የማታ ፡ የማታ(፪)


ቃልህ ፡ ይብራልኝ ፡ ጌታ(፪)
እንድኖር ፡ ሁሌ ፡ በእርጋታ
ቃልህ ፡ ይብራልኝ ፡ ጌታ(፪)

ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልማር ፡ ቃልህን
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልወቅ ፡ ቃልህን
ረቢ ፡ ሆይ(፪)

(ረቢ ፡ ሆይ) ፡ ና ፡ አስተምረኝ
(ረቢ ፡ ሆይ) ፡ በቃልህ
(ረቢ ፡ ሆይ) ፡ መንገዴን ፡ አቅና
(ረቢ ፡ ሆይ) ፡ ከሕይወት ፡ ቃልህ(፪)