አመሰግናለሁ (Amesegenalehu) - ዮሐንስ ፡ በላይ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዮሐንስ ፡ በላይ
(Yohannes Belay)

Yohannes Belay 2.jpg


(2)

ሃሳቤን ፡ ፈውሰው
(Hasaben Fewesew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሐንስ ፡ በላይ ፡ አልበሞች
(Albums by Yohannes Belay)

አመሰግንሃለሁ(፫)
ስትረዳኝ/ስትራራልኝ ፡ በዓይኔ ፡ ስላየሁ
አመሰግንሃለሁ(፪)

የሚጤሰውን ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋህም
ቅጥቅጡን ፡ ሸምበቆዬን ፡ ጌታ ፡ አልሰበርክም
የወደቀውን ፡ አይተህ ፡ መች ፡ ተውከው ፡ ጌታ
አጸናንተህ ፡ አቆምከው ፡ ሆንክለት ፡ መከታ

አመሰግንሃለሁ(፫)
ስትረዳኝ/ስትራራልኝ ፡ በዓይኔ ፡ ስላየሁ
አመሰግንሃለሁ(፪)

ዕለት ፡ ዕለት ፡ ፍቅርህ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ ፡ ነው
ጉልበት ፡ ትሆናለህ ፡ ለደካከመው
እንደ ፡ ንስር ፡ ኃይሉን ፡ ታድሰውና
ዳግም ፡ ታቆማለህ ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና

Waaqayyoo siin galatee ffadha

ስለውለታህ ፡ ላመስግንህ
ስለማዳንህ ፡ ላመስግንህ
ስለጥበቃህ ፡ ላመስግንህ
ስላደረክልኝ ፡ ላመስግንህ

ስለውለታህ ፡ ላመስግንህ
ስለማዳንህ ፡ ላመስግንህ
ስለሰራህልኝ ፡ ላመስግንህ(፪)