Yohannes Bekele/Singles/Lante Gietayie
{{SingleLyri |ዘማሪ | |ርዕስ=ለአንተ ፡ ጌታዬ |Title=Lante Gietayie |ዓ.ም.=፳ ፻ ፯ |Year=2015 |Length=10:09 |ቋንቋ=አማርኛ |Language=Amharic |Lyrics=::ለአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ምላሽ ፡ ቢሆንልህ
- ማደርግልህ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ ቢያረካልህ
- ይሄ ፡ ነው ፡ መሻቴ ፡ ለዉለታህ ፡ ሁሉ
- ሌላ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያሉ
ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ በውኑ ፡ ጌታዬ ቆጥሬ ፡ ማልጨርሰው ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ያ ፡ ብዬ ብቻ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አገለግላለሁ አሁን ፡ ከሆንኩልህ ፡ 'ሆ' ፡ በላይ ፡ እሆናለሁ (፪x)
- ለአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ምላሽ ፡ ቢሆንልህ
- ማደርግልህ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ ቢያረካልህ
- ይሄ ፡ ነው ፡ መሻቴ ፡ ለዉለታህ ፡ ሁሉ
- ሌላ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ ፡ ጌታዬ ፡ ኃያሉ/ኢየሱሴ ፡ ኃያሉ (፪x)
አሕዛብ ፡ አያውቁህም ፡ የእኔ ፡ ነፍስ ፡ ግን ፡ ታውቅሃለች የፍቅር ፡ ፊትህን ፡ በየዕለት ፡ ትናፍቃለች ያለአባትነትህ ፡ መኖር ፡ ከቶ ፡ አይሆንላትም መሳይ ፡ አጭበርባሪ ፡ ከቶ ፡ ከአንተ ፡ አይነጥሏትም (፪x)
ላመስግንህ ፡ ዛሬ ፡ የኔ ፡ ጌታ ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ስለማይቆጠር ፡ ውለታህ በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ዘለአለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ስምህ (፪x)
ሥጋዬን ፡ አልጥም ፡ ፊቴን ፡ አልቧጭርም አምላኬን ፡ ለማግኘት ፡ ብዙ ፡ አልቸገርም እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ስለው ፡ አቤት ፡ የሚለኝ ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ያለኝ
- የእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር
- የእኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚናገር
አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ የእኛማ ፡ እግዚአብሔር ፡ እኩያ ፡ የለህ አቤት ፡ ፍጥረት ፡ አይቶ ፡ ተደነቀብህ የእኔማ ፡ እየሱስ ፡ እኩያ ፡ የለህ (፬x)
አሕዛብ ፡ አያውቁህም ፡ የእኔ ፡ ነፍስ ፡ ግን ፡ ታውቅሃለች የፍቅር ፡ ፊትህን ፡ በየዕለት ፡ ትናፍቃለች ያለአባትነትህ ፡ መኖር ፡ ከቶ ፡ አይሆንላትም መሳይ ፡ አጭበርባሪ ፡ ከቶ ፡ ከአንተ ፡ አይነጥሏትም
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ከሞትም ፡ ያድናል ከሞትም ፡ ያድናል ፡ እየሱስ ከሞትም ፡ ያድነዋል ፡ ከሞትም ፡ ያድናል ከሞትም ፡ ያድናል ፡ እየሱስ (፫x)
አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ አመልካለሁ ፡ ለማንም ፡ የማይረታ አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁት አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ (፪x)
ፍቅሩን ፡ አይቼ ፡ ቀምሼዋለው ፍፁም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለው በመከራዬ ፡ እርሱ ፡ እየገባ ይጋፈጠዋል ፡ እንዳልጎዳ
አመልካለሁ ፡ ይህንን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ አመልካለሁ ፡ ለማንም ፡ የማይረታ አመልካለሁ ፡ ግንበኞች ፡ የናቁት አመልካለሁ ፡ የማዕዘን ፡ እራስ
እንግዳ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ስኖር ፡ በዚች ፡ አለም ቤቴ ፡ በሰማይ ፡ ነው ፡ በእዚህ ፡ ምንም ፡ የለኝ መላእክት ፡ ይጠሩኛል ፡ በሰማይ ፡ በር ፡ ከፍተው ከእንግዲህ ፡ ይህ ፡ አለም ፡ ፍፁም ፡ ቤት ፡ አይደለም (፪x)
ታማኝ ፡ ወዳጅ ፡ እንዳንተ ፡ እንደሌለ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ታውቃለህ ፡ እኔን ፡ የምያፅናናኝ መላእክት ፡ ይጠሩኛል ፡ በሰማይ ፡ በር ፡ ከፍተው ከእንግዲህ ፡ ይህ ፡ አለም ፡ ፍፁም ፡ ቤት ፡ አይደለም (፪x)