የምታስፈልገኝ (Yemtasfelgegn) - ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ
(Yishak Sedik)

Lyrics.jpg


(2)

Yiwedenal
(Yiwedenal)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(8)

ጸሐፊ (Writer): ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ
(Yishak Sedik
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይስሐቅ ፡ ሰዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Yishak Sedik)

ይሄ ነው ፀሎቴ ማይቀየረው
ምንም ቢሰጠኝ እጄ ማይለቀው
ጠብቄ የያዝኩት እንደ ቀሪ ሃብት
ራሴን ማገኘው ሁሌም ባንተ ፊት

አንተን ፈልጌ ነው/4

የምታስፈልገኝ አንተ ነህ/2
እኔ ምፈልገው አንተን ነው/2

እህል ውሃ አይደለም ወይም መጠለያ
ለዘላለም አንተ ነህ የእኔ መኖሪያ
የምታስፈልገኝ አንተ ነህ
የምታፈልገን አንተ ነህ

ቃልህ ህይወቴ ነው ፊትህ ብርሃኔ
የሱስ ባንተ ነውና የሆነው መዳኔ
እኔ ምፈልገው አንተን ነው/2

ይሄ ነው ፀሎቴ ማይቀየረው
ምንም ቢሰጠኝ እጄ ማይለቀው
ጠብቄ የያዝኩት እንደ ቀሪ ሃብት
ራሴን ማገኘው ሁሌም ባንተ ፊት

አንተን ፈልጌ ነው/4

የምታስፈልገኝ አንተ ነህ/2
እኔ ምፈልገው አንተን ነው/2

በውድቅት ለሊት ነፍስ ስጋዬ አርፈው
መንፈሴ ግን ላንተ ነቅቶ ነው ሚገኘው
የምታስፈልገኝ አንተ ነህ
የምታስፈልገን አንተ ነህ

አለምን ያስንቃል ሃልወትህ ገዝቶ
ካንተ ያጣብቃል ህይወት ሰማይ ገብቶ
እኔ ምፈልገው አንተን ነው/2

አንዴ ይነደሉ ቀላያት ያፍስሱ
በህይወት ወሃ ውስጥ ነፍሳት ይረስርሱ
ሰማይ ሰማያት በቃ ይከፈቱ
አንተን ለማግኘት ነው የትውልቅ ናፍቆቱ

የምታስፈልገን አንተው ነህ