From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ (Yishak Sedik)
|
|
፪ (2)
|
ይወደናል (Yiwedenal)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2018
|
ቁጥር (Track):
|
፭ (5)
|
ጸሐፊ (Writer):
|
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ (Yishak SedikProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የይስሐቅ ፡ ሰዲቅ ፡ አልበሞች (Albums by Yishak Sedik)
|
|
እገኛለሁ ላከብርህ እገኛለሁ
እኖራለሁ ላመልክህ እኖራለሁ
እገኛለሁ ላነግስህ እገኛለሁ
እሰግዳለሁ በፊትህ እሰግዳለሁ
ውዴ ሆይ ወዱ ጌታዬ ሆይ
ውዴ ሆይ እየሱሴ ሆይ
እንዳንተ የለም በምድር በሰማይ/4
ፀሎት መለመኛ ከእጅህ መቀበያ
ብቻ ማን አረገው ቅዱሱን መሰዊያ
ላመልክህ መጣለሁ ውስጤ አንተን ተርቦ
ያንተ ፍቅር ያለው አይጠግብም አግኝቶህ
ከውዶች ተወደህ ከምርጦች ተመርጠህ
በቅዱሳን መሃል ከብረህ ትኖራለህ
ከውዶች ተወደህ ከምርጦች ተመርጠህ
በልጆችህ መሃል ከፍ ከፍ ትላለህ
ለኔስ ለኔስ ለኔስ ኢየሱስ ነህ ብርቄ
ለኔስ ለኔስ ኢየሱስ ነህ ውዴ
እንዳንተ የለም በምድር በሰማይ/4
ነፃነት ያገኘ ባሪያው ልጅ ተብሎ
ዘልቆ ገብቶ ቀርቷል አንተን አንተን ብሎ
ጊዜ እና ሁኔታ ስፍራ ሳይገድበው
ፊትህ አይታጣም ፍቅርህ የማረከው
ከውዶች ተወደህ ከምርጦች ተመርጠህ
በቅዱሳን መሃል ከብረህ ትኖራለህ
ከውዶች ተወደህ ከምርጦች ተመርጠህ
በልጆችህ መሃል ከፍ ከፍ ትላለህ
ለኔስ ለኔስ ለኔስ ኢየሱስ ነህ ብርቄ
ለኔስ ለኔስ ኢየሱስ ነህ ውዴ
እንዳንተ የለም በምድር በሰማይ/4
|