From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ (Yishak Sedik)
|
|
፪ (2)
|
ይወደናል (Yiwedenal)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2018
|
ቁጥር (Track):
|
፮ (6)
|
ጸሐፊ (Writer):
|
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ (Yishak SedikProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የይስሐቅ ፡ ሰዲቅ ፡ አልበሞች (Albums by Yishak Sedik)
|
|
ካንተ ወደማን ወዴት እሄዳለሁ/4
አንተ እኮ ጌታዬ የህይወት ቃል አለህ
ኧረ አንተ እኮ እየሱስ እራስህ ህይወት ነህ
አንተ እኮ ጌታዬ የህይወት ቃል አለህ
አንተ እኮ እየሱስ እራስህ ህይወት ነህ
ካንተ የተገኘ ያላንተ አይኖርም
ህይወቱ ያረገህ እንዳንተ አያገኝም
ካንተ የተገኘ ያላንተ አይኖርም
እግርህ ስር የቀረ ከህይወት አይጎልም
አቤት አንተን ያየ የበራህለት ሰው
የልቦናው አይኖች ያስተዋሉ አጥርተው
ህይወት እየሱስ ነው ብሎ አርፎ ይኖራል
ነፍሱን ላንተ ሰቶ ካንተ የት ይሄዳል
ፈጥኖ ለሚገዛው ያለውን ሁሉ ሽጦ
የሰውርከው ክብር ያበራል ተገልጦ
በደስታ ይከታላል ያወቀ ላንተ አድሮ
የዚን አለም ምረብ እንደ ጉድፍ ቆጥሮ
አንተ እኮ ጌታዬ የህይወት ቃል አለህ
ኧረ አንተ እኮ እየሱስ እራስህ ህይወት ነህ
አንተ እኮ ጌታዬ የህይወት ቃል አለህ
አንተ እኮ እየሱስ እራስህ ህይወት ነህ
ካንተ የተገኘ ያላንተ አይኖርም
ህይወቱ ያረገህ እንዳንተ አያገኝም
ካንተ የተገኘ ያላንተ አይኖርም
እግርህ ስር የቀረ ከህይወት አይጎልም
በረሃብ በጥጋብ በማጣት በማግኘት
ያለኸኝ እየሱስ በቂ ነህ ለማለት
ሃይልን ትሰጥና ሁሉን ታስችላለህ
ነፍስ ረክታ እንድትኖት ሚያረግ ብርሃን አለህ
አለዚያማ ጌታ ፍላጎት ገደል ነው
የሞላህለት ብዙ ያፈገፈገው
መልሱን ያላገኘ ጥያቄ ቢኖረኝ
እኔ ግን ከአንተ አይችልም ሊለየኝ
አንተ እኮ ጌታዬ የህይወት ቃል አለህ
ኧረ አንተ እኮ እየሱስ እራስህ ህይወት ነህ
አንተ እኮ ጌታዬ የህይወት ቃል አለህ
አንተ እኮ እየሱስ እራስህ ህይወት ነህ
ካንተ የተገኘ ያላንተ አይኖርም
ህይወቱ ያረገህ እንዳንተ አያገኝም
ካንተ የተገኘ ያላንተ አይኖርም
እግርህ ስር የቀረ ከህይወት አይጎልም
ባላቸው ልምድ እውቀት ሌቱን ሁሉ ደክመው
አንድም አሳ አልያዙም ነበር ሲያጠምዱ አድረው
እየሱስ ግን ደርሰህ መረብ እስኪቀደድ
ረዴትክን አፈሰስክ ከታምራትህ ዘንድ
ህይወት ግን አለፈ ያጡትን ከማግኘት
ሁሉን ትተው ጌታ የተከተሉህ ለት
መለኮት አግኝቶት የሰማዩ ብርሃን
ማን እራሱ ይኖራል ካንተስ የት ይኬዳል
ካንተ ወደማን ወዴት እሄዳለሁ/4
|