From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ (Yishak Sedik)
|
|
፪ (2)
|
Yiwedenal (Yiwedenal)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2018
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፬ (14)
|
ጸሐፊ (Writer):
|
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ (Yishak SedikProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የይስሐቅ ፡ ሰዲቅ ፡ አልበሞች (Albums by Yishak Sedik)
|
|
ቀና አረገን ቀና ቀና ልጁን በኛ ገለጠና
ክብሩን በኛ ገለጠና
ይጨምራል ክብር ገና ለፀጋው ክብር ምስጋና
ለስሙ ክብር ምስጋና
ከክብር ወደ ክብር ሆኗል የኛ ነገር
በክርስቶስ የሆነልን ቃሉ እንደሚናገር
ከክብር ወደ ክብር ሆኗል የኛ ነገር
በክርስቶስ የታየልን ቃሉ እንደሚናገር
ወደፊት ነው ወደፊት ወደላይ ነው ወደላይ
ዘላለም ከብሮ ልናይ
ወደፊት ነው ወደፊት ወደላይ ነው ወደላይ
ፀጋው አርጎን የበላይ
ከሃጥያት ህግ በላይ ፀጋው አረገን የበላይ
ከሞት ፍርሃት ባላይ ፀጋው አረገን የበላይ
በአለማዊነት ላይ ፀጋው አረገን የበላይ
በጠላት ሃይል ሁሉ ላይ ፀጋው አረገን የበላይ
እራስ እንጂ ጅራት እንዳንሆን
የሚጨምር ህይወት ፀጋው ሰቶን
እለት እለት እንለወጣለን
ከክብር ወደ ክብር እንሄዳለን
አድኖ ያልተወን ፀጋው በዝቶልናል
ምኞታችን ክደን አለምን ንቀናል
የክብሩን መገለጥ ስንጠብቅ ከሰማይ
ወደ ኋላ አንዞርም ወደታችም አናይ
ከሃጥያት ህግ በላይ ፀጋው አረገን የበላይ
ከሞት ፍርሃት ባላይ ፀጋው አረገን የበላይ
በአለማዊነት ላይ ፀጋው አረገን የበላይ
በጠላት ሃይል ሁሉ ላይ ፀጋው አረገን የበላይ
ከማይጠፋው ካምላክ ዘር ተወልደን
ለምልመናል አለን በፀጋው ፀድቀን
ልክ እንደዘንባባ እናፈራለን
ገናም እንደ ዝግባ እንገዝፋለን
አድኖ ያልተወን ፀጋው በዝቶልናል
ምኞታችን ክደን አለምን ንቀናል
የክብሩን መገለጥ ስንጠብቅ ከሰማይ
ወደ ኋላ አንዞርም ወደታችም አናይ
ወደፊት ነው ወደፊት ወደላይ ነው ወደላይ
ዘላለም ከብሮ ልናይ
ወደፊት ነው ወደፊት ወደላይ ነው ወደላይ
ፀጋው አርጎን የበላይ
ፀጋው አረገን የባላይ
ፀጋው አረገኝ የበላይ
|