From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ተነስ/4
ፍጠን/2
ተነስ ፍጠን
ከተኛሁበት ቀስቅሶ መንፈሱ አቆመኝ አንስቶ
ከደነዘዝኩበት አነቃቅቶ በቃሉ ልቤን አበርትቶ
በከፍታዎች ላይ በክብር ሊያስኬደኝ
መንፈስ ቅዱስ ነጥቆ ከምድር አላቀቀኝ
በጠላቶቼ ላይ በድል ሊያራምደኝ
ከአለም ክፋት በላይ ቀብቶ አፈጠነኝ
ተነስ ተነስ አለኝ/2
ፍጠን ፍጠን አለኝ
ተነስ ፍጠን አለኝ
እልፍ ይዤ ወደኋላ መቼም ዞሬ ላላይ/2
የወንጌሉ አደራ ተሰቶኛል ከሰማይ/2
የሩጫው ሜዳ ላየ ተረኛ አድርጎኛል/2
በቀረው ልጋደል ልሮጥ ይገባኛል/2
በብቃት ላልሆነው በስጋ መበርታት
ሃይልን ተቀበልኩኝ በቅባቱ መምጣት
ለሚያምን ተችሏል ለሰው ያልተቻለ
ሁሉን ችሎ ሚያስችል መንፈስ ቅዱስ አለ
ተነስ ተነስ አለኝ/2
ፍጠን ፍጠን አለኝ
ተነስ ፍጠን አለኝ
የኋላን የሚያስተው ጌታን እያየሁኝ
የፊቴን ለመያዝ እዘረጋለሁኝ
መድረስ ግቤ ሆኖ እምነቴ ሳይጠፋ
በፅናት ሮጣለው በማያዝል ተስፋ
በብቃት ላልሆነው በስጋ መበርታት
ሃይልን ተቀበልኩኝ በቅባቱ መምጣት
ለሚያምን ተችሏል ለሰው ያልተቻለ
ሁሉን ችሎ ሚያስችል መንፈስ ቅዱስ አለ
ተነስ ተነስ አለኝ/2
ፍጠን ፍጠን አለኝ
ተነስ ፍጠን አለኝ
እንትጋና እንጨርስ ሩጫውን በድል
በመንፈሱ እንጋደል መልካሙን ገድል
ኖረን ብናልፍ የክርስቶስ ሆነን የጌታ
መዝገባችን ከምድር ይለፍ ከአለም ደስታ
ሰነፍ ስለሰው ሲያወራ በከንቱ ያልፋል
ፃድቅ ቢውድቅም ተነስቶ በድል ይደርሳል
ወገን ተነስ ቀን ሳል እንስራ ከእየሱስ ጋራ
ለጌታው ክብር የተጠራ መቼም አይፍራ
ተነስ ተነስ አለኝ/2
ፍጠን ፍጠን አለኝ
ተነስ ፍጠን አለኝ
|