መንፈስ ፡ ቅዱስ (Menfes kidus) - ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ
(Yishak Sedik)

Lyrics.jpg


(2)

ይወደናል
(Yiwedenal)

ዓ.ም. (Year): 2018
ቁጥር (Track):

(2)

ጸሐፊ (Writer): ይስሐቅ ፡ ሰዲቅ
(Yishak Sedik
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይስሐቅ ፡ ሰዲቅ ፡ አልበሞች
(Albums by Yishak Sedik)

አግኘኝ መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነትህ ምራኝ
አግኘኝ ክንድህ ታፅናኝ እጅህ ትርዳኝ

ና ዳሰኝ አረስርሰኝ ተጠምቼሃለው
ና ዳሰኝ አረስርሰኝ እፈልግሃለው
ና ዳሰኝ አረስርሰኝ ተጠምቼሃለው
ና ዳሰኝ አረስርሰኝ እፈልግሃለው

መንፈስ ቅዱስ/8

አይን ከማየት ጆሮም ከመስማት
ሞልቶ አያውቅም ለስንት ዘመናት
ምኞትን መጦም ድሎትን ማጣት
አንተ ካልረዳህ ነፍስ አይሆንላትም

ግና መንፈሴ ሲጮህ ወዳንተ
እኔ ይሰማኛል እየቃተተ እየቃተተ
አልጥምህ ብሎኝ ምቾቴ ሁሉ
አካላቴ ጭምር መንፈስ ህን አሉ
አንተን አንተን አሉ

መንፈስ ቅዱስ/8

ና ዳሰኝ አረስርሰኝ ተጠምቼሃለው
ና ዳሰኝ አረስርሰኝ እፈልግሃለው
ና ዳሰኝ አረስርሰኝ ተጠምቼሃለው
ና ዳሰኝ አረስርሰኝ እፈልግሃለው