From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ሰማይ ምድር ባንተ ነው ሁሉ የሆነው
ሰማይ ምድር ሁሉ ባንተ ነው ሆኖ የተገኘው
ካንተ ነው ባንተ ነው ሁሉ የሆነው
ካንተ ነው ባንተ ነው የተፈጠረው
ካንተ ነው ባንተ ነው ሁሉ የሆነው
ካንተ ነው ባንተ ነው የተፈጠረው
የሰማይ ሰራዊት እንዳፍህ ቃል ሆኑ
ልክ እንደተናገርክ በየስፍራቸው ፀኑ
ያለምንም እንዲያው ሲገኝ አጥናፍ አለም
ከፍጥረታት መሃል ባንተ ያልሆነ የለም
ዙፋንህን ሰማይ አርገህ
ምድርንም በክብርህ ሞልተህ
እኛም በቃልህ ተወልደን
ልናመልክህ ተፈጥረን
ክበር እንላለን ስግደት ላምላካችን
ይገባሃልና እየሱስ ጌታችን
ክበር እንላለን ስግደት ላምላካችን
ይገባሃልና እየሱስ ጌታችን
ሰማይ ምድር ባንተ ነው ሁሉ የሆነው
ሰማይ ምድር ሁሉ ባንተ ነው ሆኖ የተገኘው
ካንተ ነው ባንተ ነው ሁሉ የሆነው
ካንተ ነው ባንተ ነው የተፈጠረው
ካንተ ነው ባንተ ነው ሁሉ የሆነው
ካንተ ነው ባንተ ነው የተፈጠረው
የሚታየው ሁሉ ተፈጥሮ የታየው
መንፈስ ከሆንክ አምላክ ስለፍቃድህ ነው
የሌለውን ነገር ልክ እንዳለ ጠርተህ
የነበረ እስኪመስል በቃልህ አስቀምጠህ
ዙፋንህን ሰማይ አርገህ
ምድርንም በክብርህ ሞልተህ
እኛም በቃልህ ተወልደን
ልናመልክህ ተፈጥረን
ክበር እንላለን ስግደት ላምላካችን
ይገባሃልና እየሱስ ጌታችን
ክበር እንላለን ስግደት ላምላካችን
ይገባሃልና እየሱስ ጌታችን
|