የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ (Yegid Tasfelegeghaleh) (9) - ይድነቃቸው ተካ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ይድነቃቸው ተካ
(Yidnekachew Teka)

Lyrics.jpg


(2)

አልበም
(ኢየሱስ)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2016/2023)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6፡16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ትልቅ ፡ ቦታ
በምንም ፡ አልተካው ፡ የኔ ፡ እድል ፡ ፈንታ
ላንተ ፡ አብሮነት ፡ ያለኝ ፡ ትልቅ ፡ ቦታ
በምንም ፡ አልተካው ፡ የኔ ፡ እድል ፡ ፈንታ

የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የምሬን ፡ ነው ፡ ታስፈልገኛለህ

ሰው ፡ እንዴት ፡ ትንሽ ፡ ነው
ብቻውን ፡ ከወጣ ፡ ያላንተ
ቀትረ ፡ ቀላል ፡ ሆኖ
ይኖራል ፡ ሁሌ ፡ እንደዋተተ

ግን ፡ አብሮህ ፡ ያለ ፡ ሰው
መንፈስህ ፡ ያጀበው ፡ ከኋላ
ሕዝብን ፡ ይታደጋል
በእየሱስ ፡ ምድርን ፡ እየሞላ

በህይወቴ ፡ የነገርከኝ
ያስጀመርከኝ ፡ መንገድ
ብቻዬን ፡ አልደፍረውም
መንፈስህ ፡ ነው ፡ የግድ

በሰው ፡ አፍ ፡ ብቻ ፡ አውርቼ
አይደለም ፡ የማሳምነው
ወይ ፡ ከእግረኛ ፡ ጋር ፡ ሮጬ
ልድረስበት ፡ የምለው

መኖር ፡ አልችልም ፡ ያላንተ
እኔ ፡ አለመድኩም ፡ ያላንተ
አገልግሎትም ፡ ያላንተ
አይሞከርም/አይደፈርም ፡ ያላንተ
(፪x)

የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የምሬን ፡ ነው ፡ ታስፈልገኛለህ

አይቀልብኝ ፡ ጌታ ፡ አብሮነትህ
ጌታ ፡ አብሮነትህ
እኔ ፡ አልለምደውም
እየሱስ ፡ አብሮነትህን
ጌታ ፡ አብሮነትህን

የኔ ፡ ሞገስ ፡ ክብሬ (አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ)
የኔ ፡ ማስፈራቴ (አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ)
እሩቅ ፡ የምሄድብህ (አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ)
መቼም ፡ የማልቆምብህ (አንተ ፡ ነህ ፡ አንተ)


እኔ ፡ የለመድኩት (ከአንተ ፡ ጋር)
የእውነት ፡ የምኖረው (ከአንተ ፡ ጋር)
አገልግሎቴ (ከአንተ ፡ ጋር)
መቼም ፡ የማይቆመው (ከአንተ ፡ ጋር)
ሀገር ፡ የሚሰማኝ (ከአንተ ፡ ጋር)
ምድርን ፡ የምወርሰው (ከአንተ ፡ ጋር)
ጠላት ፡ የሚፈራኝ (ከአንተ ፡ ጋር)
የማልለመደው (ከአንተ ፡ ጋር)

የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የግድ ፡ ታስፈልገኛለህ
የምሬን ፡ ነው ፡ ታስፈልገኛለህ

ጣልቃ ፡ የማትገባበት ፡ የማትሳተፍበት
የሕይወቴ ፡ ክፍል ፡ የለም
አንተን ፡ የማያካትት
እውቅና ፡ እሰጥሃለሁ ፡ በነገሬ ፡ ሁሉ ፡ ላይ
ዘንግቼህ ፡ አቅም ፡ የለኝ
የት ፡ ልሄድ ፡ አንተን ፡ ሳላይ