በደም ፡ ያጌጠ (Bedem yagete) (8) - ይድነቃቸው ተካ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ይድነቃቸው ተካ
(Yidnekachew Teka)

Yidnekachew Teka 2.jpg


(2)

Eyesus
(Eyesus)

ዓ.ም. (Year): (2023)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

ከወደቅሁበት አዘቅት መጥተህ የክብርህን ጥግ አሳየኸኝ
 የለበስኩትን የውርደት ሸማ
 ከላዬ ወርዱል ኢየሱስ በግርማህ
 ለበስኩትን የውርደት ሸማ
 ከላዬ ወድቋል ኢየሱስ በግርማህ

 እንኳን ያንተ ሆንኩ እንኳን ያንተ ኢየሱሴ (2x)
 ክብርን ያወኩት ባንተ አደል ወይ መች በራሴ
 ወግ ማዕረግ ቢሉኝ የለመድኩት ባንተ እጅ ነው (2x)
 የክብር ልብሱን ያለበሰኝ ምህረትህ ነው

 አክሊል እንደለበሰች እንደ ሙሽራ
 በጌጥ እንደ ተዋበች እጅጉን አምራ
 ኢየሱስ የማዳን ልብስ አለበስከኝ
 መጎናጸፊያ የጽድቅ ደረብክልኝ

 ክበርልኝ (6x)

 ይኽው አነሳኝ እጅህ (2x)
 ይኽው አነጻኝ ደምህ (2x)
 በደምህ ያጌጥ ልብሴ (2x)
 አንተ ነህ ኢየሱሴ (2x)

 የእንደገና ሞገሴ (4x)
 የምረት ታሪኬ (4x)

 ይታዘቡኛል እኔስ ብኮራ
 የሚያውቁኝ ሁሉ እያለሁ ተራ
 እዚህ ግባ እንኳን የማይሉትን ሰው
 የምህረት እጅህ አነሳኝ ይኽው
 አያምርብኝም ዝም ብል ዛሬ
 በእልልታ ዜማ ልጩህ ለክብሬ

 ክብሬ አንተ ነህ ኢየሱስ
 በአደባባይ ኢየሱስ
 የማሳይህ ኢየሱስ
 አገር እንዲያይ ኢየሱስ

 የእንደገና ሞገሴ (2x)
 የምህረት ታሪኬ ነህ (2x)

 በኃጢያት ተገኘች ብለው ይዘዋት
 እያሰቃዩ ወደ አንተ አመጧት
 እኛስ ብለናል ትገደል አሉ
 ፈሪሳውያን ድንጋይ ይዘው
 አንተ ስለሱዋ ምን ትላለህ
 ተናገር ሲሉ ምህረት አወጂህ

 አንተም ለኔ ኢየሱስ
 ያልክልኝ ነው ኢየሱስ
 ዘላለሜን ኢየሱስ
 የቀየረው ኢየሱስ

 የእንደገና ሞገሴ (2x)
 የምህረት ታሪኬ ነህ (2x)