ላውድልህ ፡ ሀገሩ (Lawudeleh Hagerun) (4) - ይድነቃቸው ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ተካ
(Yidnekachew Teka)

Lyrics.jpg


(2)

ኢየሱስ
(Eyesus)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ ((2005))
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

ምድር ላይ ካለው ነገር
ትልቅ ተብሎ ከሚነገር
ሰው ሁሉ ከሚያየው ከፍ አድርጎ
ለኔ ግን ኢየሱስ ደስታዬ ነህ አብሮነትህ
ይፈስሳል እምባዬ አይቆምም ኢየሱስ ሳይህ
የቱም ነገር ከልቤ አይደርስም ካንተ ሌላ
የኔ ንጉስ ነገሰኸ ቀረህ ልቤን ገዝተህ በቃ
ሞላህበኝ አይኔን ባንተ ብቻ ሌላ እንዳላይ
የአለም ክብር ደብዝዞ ጠፋብኝ እኔ አንተን ሳይ
 ኢየሱስ *5
እኔ አልችልም ወዳአለች እቺ ነፍሴ
አቅም የለኝ ወዴት ልሄድ ከእስትንፋሴ

አንተን አጥቼ መኖር ለኔ ከቶ አይሆንልኝ
ምን ሊተርፈኝ ከዚያ ኸረ ምንስ ሊቀረኝ
አንተ ባትኖር ሕይወቴ ላይ ምን ስለኔ ይወራል
ከምናምንቴነት ፍቅርህ ቀንሶኛል
ልክደው በማልችል መንካት ነክተኸኛል

  ካንተ ወዴት ካንተ
ካንተ የት እሄዳለሁ
የሕይወት ውኃ እንጀራዬ የት እሄዳለሁ
አንተ አይደለህ ወይ ሰላሜ
አንተ አይደለህ ወይ እረፍቴ
አንተ አይደለህ ወይ ደስታዬ
አንተ አይደለህ ወይ ሞገሴ


እግርህ ስር ተደፍቼ
የልቤን ሸቶ ሰብሬ
ይቀየር የቤቱ መዐዛው
ላውድልህ ሀገሩን ምድሩን ባንተ ፍቅር
በየቤቱ ኢየሱስ የሚለው ስም እንዲዘመር
የሚሰማኝ የሚያየኝ በሙሉ ይውደድህ
ጨርቁን ጥሎ ልክ እንደ አበደ ሰው ይሁንልህ
የኔ ስራ አንተን ማስወደድ ነው በሄድኩበት
ኢየሱስ ስል እየታየኽልኝ በቆምኩበት

ክብርህን እንዲሸከም ስትፈልግ ደካማ ሰው
እኔ ተገኘሁኝ ከሁሉ ኃጢያተኛው
አንተ እጅ ላይ ካልዋለ ለምንም የማይሆን
ምልክት አደረከው ማሳያ ክብርህን
የምሕረትህ ዕቃ ገለጥክብኝ ራስህን

ካንተ ወዴት ካንተ
ካንተ የት እሄዳለሁ
የሕይወት ውኃ እንጀራዬ የት እሄዳለሁ
አንተ አይደለህ ወይ ሰላሜ
አንተ አይደለህ ወይ እረፍቴ
አንተ አይደለህ ወይ ደስታዬ
አንተ አይደለህ ወይ ሞገሴ

ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ *2
የልቤ ውዱ ተባረክ
የቤቴ ውዱ ተባረክ
የአሳቤ ውዱ ተባረክ
የሕይወቴ ውዱ ተባረክ