From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይድነቃቸው ተካ (Yidnekachew Teka)
|
|
፪ (2)
|
አልበም (2)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፲ ፩ (2016)
|
ቁጥር (Track):
|
፫ (3)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:31
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የይድነቃቸው ተካ ፡ አልበሞች (Albums by Yidnekachew Teka)
|
|
ደካማ ሆኜ አገኘኸኝ
ኃጥያተኛ ሆኜ አገኘኸኝ
የማልጠቅም ሆኜ አገኘኸኝ
ከሰይጣን እጅ ሆኜ አገኘኸኝ
ግን ባንተ ከዚህ ሁሉ ወጥቻለሁ
ግን ባንተ የእግዚአብሔር ልጅ ተብያለሁ
ግን ባንተ ከዚህ ሁሉ ወጥቻለሁ
ግን ባንተ የእግዚአብሔር ልጅ ተብያለሁ
ዛሬ አርገኸኛል የብርሃን ልጅ እኔን
እየሱስ ወሰደህ ጨለማዬን (X4)
ይቺ ፅዋ ከኔ ትለፍ ብትል እንኳ
እየሱስ ታዘሃል እንዳያልፈኝ የሕይወት ፅዋ
የእግዚአብሔር በግ አስቀድመህ የታረድከው
ሌባው እንዳያርደኝ እንዳልጠፋ እንዳልሞት ነው
ለምን ተውከኝ ብለህ ስትጮህ አብ ዝም ያለህ
እኔ እንዳልጣል እንዳልተው ሁሌ ፊትህ
ደዌ ህመሜን ተቀበልህ ተሸከምህ
እኔ ያንተን ሕይወት ደኅንነትን እንድቀበል
የብርሃን መልዕክቴ ነህ እየሱስ ልቤ ላይ በራህ
ሰማሁህ የምስራቼ ድኛለሁ ወንጌል ሰምቼ
በአመድ ፈንታ ሆነኽልኛል አክሊሌ
በለቅሶ ፈንታ የደስታ ዘይት ነሆ ለኔ
በሃዘን ፈንታ የደስታ መጎናፀፊያ
አረከኝ እኔን የምሕረትህ ማሳያ
ጋሻ ሆነህ ግን ተወጋህ ጎንህን
እረኛ የሆንከው ልክ እንደ በግ ተነዳህ
የአለም ጌታ በምድር ጌታ ፊት ቆመሀል
ምንጭ የሆንከው አንተ የኔ እየሱስ ተጠምተአል
እንደ ፀሐይ የሚያበራ ፊት እያለህ
ግን እኔ እንዳበራ እንድደምቅ ተተፋብህ
ሰማይ ምድርን የምትጠቀልል ልክ እንደ ጨርቅ
ግን እየሱስ ለኔ ተጠቅልለህ መቃብር ሆንክ
ይሁን ስትል የሚሆንልህ
አንተ ላይ ይሁን አሉብህ
ግን ዝም አልክ አልመለስክም
አይተህ ነው እኔን ደስታህን
ለወጉህ እጆች ኃይላቸው ነበርክ ፈጣሪ
ለሰደቡህ አፎች አንተ ነህ የእነርሱ ሰሪ
ፈቀድክላቸው አልከለከልካቸውም
የምትሞተው በጦር ለወጉህ ለእነርሱም
|