የክብሬ ፡ ደጋሽ (Yekbre Degash) (2) - ይድነቃቸው ተካ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ይድነቃቸው ተካ
(Yidnekachew Teka)

Lyrics.jpg


(2)

አልበም
(2)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ ((2005))
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

ያለቀለት ጉዳይ የሞተ
ጠላት የደገሰው ውርደት
ለክብር ቀየረው ጌታ መጥቶ
  ጌታ መጥቶ ሞት የለም ብሎ
ለከፍታ አረገው ጌታ መጥቶ
ጌታ መጥቶ እኔ አለው ብሎ

ኢየሱስ የክብሬ ደጋሽ
በጠራሁት ጊዜ ደራሽ
ሌላ ክረምት የለም በቃ አለኝ
 በቃ አለኝ አሻገረኝ
ሌላ ስጋት የለም በቃ አለኝ
  በቃ አለኝ አሳለፈኝ


ያለቀለት ጉዳይ የሞተ
ጠላት የደገሰው ውርደት
ለክብር ቀየረው ጌታ መጥቶ
  ጌታ መጥቶ ሞት የለም ብሎ
ለከፍታ አረገው ጌታ መጥቶ
ጌታ መጥቶ እኔ አለው ብሎ

ኢየሱስ የክብሬ ደጋሽ
በጠራሁት ጊዜ ደራሽ
ሌላ ክረምት የለም በቃ አለኝ
 በቃ አለኝ አሻገረኝ
ሌላ ስጋት የለም በቃ አለኝ
  በቃ አለኝ አሳለፈኝ

በቃ አለፈ
       አለፈ
የማያልፍ የሚመስለው አለፈ
              በቃ አለፈ
              አለፈ
             የማያልፍ የሚመስለው አለፈ
አለፈ *3
እለፍ ሲለው አለፈ
                    አለፈ*2
በቃ ሲለው አለፈ
                  አለፈ*2


ዮሴፍ ሞተ ብለው አሉ
                   ብለው አሉ
አበቃለት የለም አሉ
                የለም አሉ
ልብሱን በደም ነክረው መጡ
                        ነክረው ወጡ
በማስረጃ ሊያስረግጡ
                ሊያስረግጡ
እውነትም ልብሱ የዮሴፍ ነበረ
ደሙ የማን ነው እሱ በህይወት አለ
በእኔም እንዲህ ነው የሆነው ነገሩ
ሞቴን አውርተው መኖሬን

ማነው አሉ ኢየሱስ ነው አሉ
ያከበረው ኢየሱስ ነው አሉ
ይህን ያረገው ኢየሱስ ነው አሉ
ኢየሱስ ነው አሉ*5

ጠላቴ ማያስቆመው ሰው እኔ ነኝ
ጠላት እልል ማይልበት ሰው እኔ ነኝ
በአምላኩ የተረዳ ሰው እኔ ነኝ
ክብር የደገሰለት ሰው እኔ ነኝ
እኔ ነኝ በኢየሱስ ስም የዳኩኝ
እኔ ነኝ ኢየሱስ ከሞት ያዳነኝ
እኔ ነኝ ከሞት አፍ ያመለጥኩኝ
እኔ ነኝ በኢየሱስ የተረፍኩኝ
በወጀቡ ላይ ኢየሱስ
ጌታ ነውና ኢየሱስ
ስሙን ስጠራ ኢየሱስ
ማዕበሉ ሰማ ኢየሱስ
                        በወጀቡ ላይ ኢየሱስ
                        ጌታ ነውና ኢየሱስ
                     ስሙን ስጠራ ኢየሱስ
                    ማዕበሉ ሰማ ኢየሱስ
ኸረ እስኪ በማን ተረጋጋ ያሁሉ ወጀብ ወዴት ገባ
ኸረ እስኪ በማን ቤቱ ስም የተጠበቅሁት በሰላም
ኸረ እስቲ በማን የኔ ሕይወት የነፋሱ ኃይል የጠፋበት
ኸረ እስቲ በማን በማን ስም ነው
ጠላት ሕይወቴን ያላገፕው
  እኔ የማውቀው እኔ የማውቀው ኢየሱስ
  ስል ወዲያው ሰይጣን መተንፈስ ሲያቅተው
 እኔ የማውቀው እኔ የማውቀው ይህን ስም ስጠራ ጠላት ደንብሮ ሲሄድ ነው
እኔ የማውቀው እኔ የማውቀው ኢየሱስ ብዬ ወጀብ ፀጥ ሲልልኝ ነው
እኔ የማውቀው እኔ የማውቀው ኢየሱስን ስጠራው ለኔ ፀጥታ ሲሆን ነው
        እኔ ነኝ በኢየሱስ ስም የዳንኩኝ
        እኔ ነኝ ኢየሱስ ከሞት ያዳነኝ
እኔ ነኝ ከሞት አፍ ያመለጥኩኝ
እኔ ነኝ በኢየሱስ የተረፍኩኝ
በወጀቡ ላይ ኢየሱስ
ጌታ ነውና ኢየሱስ
ስሙን ስጠራ ኢየሱስ
ማዕበሉ ሰማ ኢየሱስ
                        በወጀቡ ላይ ኢየሱስ
                        ጌታ ነውና ኢየሱስ
                     ስሙን ስጠራ ኢየሱስ
                    ማዕበሉ ሰማ ኢየሱስ