Yidnekachew Teka/Eyesus/13

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የማይታለፍ ፡ ይመስል ፡ ነበር
ግን ፡ አሳለፈኝ ፡ አምላኬ ፡ እግዚአብሔር
ክብሩ ፡ እንደ ፡ ጋሻ ፡ ሆኖ ፡ ከለለኝ
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ለኔስ ፡ በዛልኝ

የኔ ፡ ሞገስ ፡ አየጨመረ
የኔ ፡ ሕይወት ፡ እየደመቀ
የኔ ፡ ነገር ፡ እየበረታ
የኔ ፡ ሰላም ፡ በዛ ፡ በጌታ

የኔ (የኔ ፡ የኔ)
የኔ ፡ ሞገስ (እየጨመረ)
የኔ ፡ ሕይወት (እየደመቀ)
የኔ ፡ ሰላም (እየጨመረ)
(፪x)

ላልሰማው ፡ አሰማ ፡ አለብኝ ፡ ልቤ ፡ ይሄ ፡ ልቤ
አትሄድም ፡ ለሚልህ ፡ ተናገር ፡ አለኝ ፡ በል ፡ አለኝ

ሌላ ፡ ሌላ ፡ ቃል ፡ አለ ፡ ትሄዳለህ (እኔን ፡ ያለ)
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ቃል ፡ አለ ፡ ትሄዳለህ (እኔን ፡ ያለ)
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ድምፅ ፡ አለ ፡ ክብር ፡ አለ (እኔን ፡ ያለ)
ኧረ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ድምፅ ፡ አለ ፡ ሞገስ ፡ አለ (እኔን ፡ ያለ)

እኔን ፡ ያለ
እኔን ፡ ያለ
እኔን ፡ ያለ
እኔን ፡ ያለ
እኔን ፡ ያለ
እኔን ፡ ያለ

ትሄዳለህ (እኔን ፡ ያለ)
ክብር ፡ አለ (እኔን ፡ ያለ)
ሞገስ ፡ አለ (እኔን ፡ ያለ)
ትበዛለህ (እኔን ፡ ያለ)

የእሳት ፡ ቅጥር ፡ ነው ፡ በዙሪያዬ ፡ አሆ
በውስጤ ፡ ክብር ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ አሆ
ጠላት ፡ ሊገፋኝ ፡ ሲሞክር ፡ አህህ ፡ ሲሞክር
ራሱ ፡ ወደቀ ፡ እግሬ ፡ ስር

የቀኙ ፡ ግርማ ፡ የክንዱ ፡ ክብር
አለ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ አጥሮት ፡ ዙሪያዬን
ሊቀርብ ፡ አልቻለም ፡ ጠላቴ ፡ ደፍሮ
ክብሩ ፡ ስላለ ፡ እንዴት ፡ ተብሎ

አይሰማም ፡ ለቅሶ ፡ ቤቴ
አስቆኛል ፡ አንዴ ፡ አባቴ
ጠላቶቼ ፡ ለቅሶ ፡ ሲሹ
ሳቄን ፡ ሰምተው ፡ ወዲያው ፡ ሸሹ
ወዲያው ፡ ሸሹ

ባረከና ፡ በራረከኝ
ታላቅነት ፡ ጨመረብኝ
አገኘና ፡ ብቻዬን
እንዲህ ፡ አለኝ
ሀገር ፡ ነህ ፡ ሀገር ፡ ነህ
ሕዝብ ፡ ነህ ፡ ሕዝብ ፡ ነህ

(አሆ) እኔን ፡ ያለ
(አሆ) እኔን ፡ ያለ
(አሆ) በዙሪያዬ
(አሆ) የእሳት ፡ ቅጥር
(አሆ) ሆኖልኛል
(አሆ) ውስጤም ፡ ክብር
(፪x)

አልሰራብኝም ፡ የእርሱ ፡ መርዶ ፡ አሆ
አባት ፡ እግዚአብሔር ፡ ወዴት ፡ ሄዶ ፡ አሆ
ተጠብቆልኝ ፡ ቀን ፡ ለሊቴ ፡ አህህ ፡ ቀን ፡ ለሊቴ
ወደኔ ፡ አይቀርብም ፡ ያ ፡ ጠላቴ

የዜማ ፡ ዕቃዬ ፡ ይነሳ ፡ ለእርሱ
ቅኔው ፡ ይደርደር ፡ ይክበር ፡ ንጉሱ
በአጠገቤ ፡ ሺህ ፡ በቀኜ ፡ አስር ፡ ሺህ
ጣልኩኝ ፡ በስሙ ፡ ሆንኩኝ ፡ ድል ፡ ነሺ

አይሰማም ፡ ለቅሶ ፡ ቤቴ
አስቆኛል ፡ አንዴ ፡ አባቴ
ጠላቶቼ ፡ ለቅሶ ፡ ሲሹ
ሳቄን ፡ ሰምተው ፡ ወዲያው ፡ ሸሹ
ወዲያው ፡ ሸሹ

ባረከና ፡ በራረከኝ
ታላቅነት ፡ ጨመረብኝ
አገኘና ፡ ብቻዬን
እንዲህ ፡ አለኝ
ሀገር ፡ ነህ ፡ ሀገር ፡ ነህ
ሕዝብ ፡ ነህ ፡ ሕዝብ ፡ ነህ

(አሆ) እኔን ፡ ያለ
(አሆ) እኔን ፡ ያለ
(አሆ) በዙሪያዬ
(አሆ) የእሳት ፡ ቅጥር
(አሆ) ሆኖልኛል
(አሆ) ውስጤም ፡ ክብር
(፪x)