ስምህ ( Semeh) (10) - ይድነቃቸው ተካ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ይድነቃቸው ተካ
(Yidnekachew Teka)

Lyrics.jpg


(2)

ኢየሱስ
(Jesus)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ ((2023))
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5፡05
ጸሐፊ (Writer): ይድነቃቸው
(Yidnekachew
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የይድነቃቸው ተካ ፡ አልበሞች
(Albums by Yidnekachew Teka)

ኢየሱስዬ ስልህ ይከበኛል ሰላምህ
ኢየሱስዬ ስልህ ይከበኛል ሞገስህ 4x

     የቱም ስም ሊለመድ ይችላል
     ሃይል ያለዉ ስም ሊደክም ይችላል
     ጠቢቡ ስም ድንገት ሞኝ ይሆናል
     ጉልበት ያለዉ ሃይሉ ይክደዋል
          የማይደክም ስም የሚያረጅ
          ክብሩ ማይነጥፍ እስከ ልጅ ልጅ
          መንፈሱን ልኮ አብ ያከበረው
          የተቀባ ስም ኢየሱሴ ነው
     ስምህ ቅባት አለው ጌታ
     ስምህ እሳት አለው ጌታ
     ስምህ መንፈስ አለው ጌታ
     ስምህ ክብር አለው ጌታ
     በስምህ ሃገር ይቀየራል
     በስምህ ከተማ ይድናል
     በስምህ መቃብር ይከፈታል
     በስምህ የሞተው ይነሳል

ከሰማይ ከገናናው ክብር
ድምፅ ወጣ ከአባቴ እግዚአብሔር
ምወድው ያከበርኩት ልጄ
ኢየሱስ ነዉ የሾምኩት ፈቅጄ
     ሙሴን አይደለም ወይም ኤሊያስን
     ስሙት አብ ያለው ጌታ ኢየሱስን
     ፍጥረት በሙሉ ያን ስም ስምቶ
     ይታዘዘዋል ክብሩን ፈርቶ

ስምህ ቅባት አለው ጌታ
ስምህ እሳት አለው ጌታ
ስምህ መንፈስ አለው ጌታ
ስምህ ክብር አለው ጌታ
በስምህ ሃገር ይቀየራል
በስምህ ከተማ ይድናል
በስምህ መቃብር ይከፈታል
በስምህ የሞተው ይነሳል

     ምላስ ሁሉ ይመስክራል
     ጉልበት ያለው ይንበረከካል
     አለቅነት ሃይላት ስልጣናት
     ሁሉም ያውቀዋል የአንተን ጌትነት
ጨለማ የሚሰማው ስም ኢየሱስ 2x
ችግር የሚሰማው ስም ኢየሱስ 2x
ተፈጥሮ የሚገዛለት ኢየሱስ 2x
አጋንንት የሚሰግድለት ኢየሱስ 2x
በስምህ አጋንት ይወጣል
በስምህ ከሞት ይመለጣል
በስምህ ታሪክ ይቀየራል
በስምህ ጨለማ ይበራል
ኢየሱስ 6x
ኢየሱስ ኢየሱስ ክርስቶስ
ኢየሱስ የተቀባው ንጉስ